የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ለሠራተኞቹ የጋራ የኢፍጣር መርሃ-ግብር አከናወነ
#ethiopia | የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ለእስልምና እምነት ተከታይ አመራሮችና ሠራተኞቹ ያዘጋጀው የጋራ የረመዳን የኢፍጣር መርሃ-ግብር መጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።
በዝግጅቱ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ክብርት ሸዊት ሻንካን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
የባህልና ቋንቋ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ነፊሳ አልማህዲ በመርሃ-ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የኢፍጣር ዝግጅቱ ዋና ዓላማ በብዝሃ ባህልና በብዝሃ ሃይማኖት መካከል ያለውን አብሮነት፣ መከባበርና ወንድማማችነት ይበልጥ ለማጠናከር መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ ሁኔታ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ውስጥ ያለውን የቆየ የመቻቻል እሴት የሚያሳይ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ክብርት ሸዊት ሻንካ በበኩላቸው፣ እንዲህ ያሉ የተቋም ደረጃ የኢፍጣር ፕሮግራሞች በሠራተኞች መካከል ያለውን መተሳሰብና መደጋገፍ እንደሚያጎለብቱ ገልጸዋል።
ሚኒስትሯ ለእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ፣ በረመዳን ወር ለአቅመ ደካሞች የሚደረጉ የማዕድ ማጋራት ሥራዎች በቀጣይነት መጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የዕለቱ ተሳታፊ አመራሮችና ሠራተኞች በበኩላቸው፣ እንዲህ ዓይነት መድረክ መዘጋጀቱ በመካከላቸው ያለውን እህትማማችነትና ወንድማማችነት ከማጠናከሩ ባሻገር፣ በሥራ ተነሳሽነታቸው ላይ አወንታዊ ተፅዕኖ እንደሚፈጥርላቸው በመግለጽ ለተቋሙ ምስጋና አቅርበዋል።
#getu #ethiopia #ramadan #iftar #cultureandsport #addisababa #የጋራኢፍጣር #ባህልናስፖርት #አብሮነት #ጌጡተመስገን #getutemesgen

5 months ago