Logo
SeledaPost
ሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫዋን ተነጠቀች!

የታራንጋ አምበሶቹ አሳክተውት የነበረው የአፍሪካ ዋንጫ ለአትላስ አምበሶቹ አሳልፎ እንዲሰጥ ካፍ (CAF) ወስኗል። ይህ ውሳኔ በብዙዎች ዘንድ "ዘመን የማይሽረው አስቂኝ ውሳኔ" እየተባለ ይገኛል።

በቅርቡ በሞሮኮ አስተናጋጅነት በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ፣ ሴኔጋል ሞሮኮን አሸንፋ ዋንጫውን ማንሳቷ ይታወሳል። በፍጻሜው ዕለት በተፈጠረ ውዝግብ ምክንያት ጨዋታው ለ17 ደቂቃ ተቋርጦ የነበረ ሲሆን፣ ጨዋታው እንደገና ከተጀመረ በኋላ ብራሂም ዲያዝ የፍፁም ቅጣት ምቱን ሆን ብሎ መሳቱን ተከትሎ፣ ሴኔጋል በፓፓ ጌ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 አሸንፋ ነበር።

የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በፍጻሜው ዕለት የተፈጠረውን ውዝግብ መነሻ በማድረግ ለካፍ ይግባኝ ሰሚ ቦርድ ቅሬታውን አቅርቦ ቆይቷል። ጉዳዩን ሲመረምር የቆየው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ይግባኝ ሰሚ ቦርድ፣ በአፍሪካ ዋንጫ ደንብ አንቀጽ 84 መሠረት የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ተሸናፊ ሆኖ እንዲመዘገብ ወስኗል።

በዚህም መሠረት የጨዋታው ውጤት የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን 3 ለ 0 አሸናፊ ሆኖ እንዲመዘገብና ዋንጫውም ለሞሮኮ እንዲሰጥ ተወስኗል። ከእግር ኳስ ቤተሰቡ ዘንድ "ለካ ለዚህ ነው 'ባንዳው' የተባለው፤ ብራሂም ዲያዝ የፍፁም ቅጣት ምቱን ባይስተው ይሻል ነበር" የሚሉ አስተያየቶች እየተሰሙ ይገኛሉ።

ሴኔጋል ጉዳዩን ለዓለም አቀፉ የስፖርት የግልግል ፍርድ ቤት (CAS) መውሰድ አለባት የሚል እምነት በሰፊው ይንጸባረቃል። "በሜዳ ላይ አሸንፈህ ዋንጫ ተሰጥቶህ፣ በጓሮ በር ዋንጫ መነጠቅ አግባብ አይደለም" የሚሉ ወገኖች፣ የአፍሪካ እግር ኳስ አሁንም መብሰል የሚቀረውና በቧልተኛ አመራሮች የተሞላ መሆኑን ማሳያ ነው በማለት ቅሬታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።

seledadotio
seledadotio
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.