ሴኔጋል ዋንጫዋን ተቀማች
ሞሮኮ የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON) አሸናፊ መሆኗን ካፍ አስታወቀ
በሞሮኮ አስተናጋጅነት በተካሄደው የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ በተፈጠረ ውዝግብ ዙሪያ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ አስገራሚ ውሳኔ አሳልፏል። ሴኔጋል በቅጣት ጨዋታውን እንደተሸነፈች ተወስኖባታል።
በዚህም መሰረት አዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ በአስተዳደራዊ ውሳኔ የውድድሩ አሸናፊ እና የዋንጫው ባለቤት ሆናለች።
የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (FRMF) ያቀረበውን ይግባኝ ለመመርመር የተሰበሰበው የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የዲሲፕሊን ኮሚቴው ቀደም ብሎ ያስተላለፈውን ውሳኔ ሽሮታል።
ባለስልጣናቱ የአፍሪካ ዋንጫ ደንብ አንቀጽ 82 እና 84ን በመጥቀስንየሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ያሳየው ባህሪ ጠንካራ ቅጣት የሚያስቀጣ ነው በማለት ወስነዋል።
በዚህም ምክንያት ሴኔጋል በፍፃሜው ጨዋታ በሽንፈት (Forfeit) እንዲሰናበት ተደርጓል። በመሆኑም ይፋዊው ውጤት ሞሮኮን 3 ለ 0 አሸናፊ በሚያደርግ መልኩ ተመዝግቧል።

5 months ago