ዓሊ ላሪጃኒ፡ በኢራን ውስጥ እጅግ ሀያል ሰው የነበሩት ለምንድን ነው?
ያሳደጋቸውስ "ስርወ-መንግስት" የትኛው ነው?
በሀገር ውስጥ ጥንካሬን፣ በውጭ ሀገር ደግሞ ብልሃተኛ ዲፕሎማሲን የያዘው የእርሳቸው ማንነት፣ በኢራን የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ ቁልፍ ተዋናይ አድርጓቸዋል።
ለብዙ ዓመታት ከጀርባ ሆነው ይንቀሳቀሱ ነበር። ድምፃቸው የጎላ ባይሆንም፣ በጣም ጠንካራው ሰው እርሳቸው ነበሩ። ትልልቅ ውሳኔዎች በሚተላለፉበት ቦታ ሁሉ ሁልጊዜም ይገኛሉ። አሁን ግን እስራኤል በእርሳቸው ላይ ግድያ መፈጸሟን አስታውቃለች፤ ይህ እውነት ከሆነ ለኢራን አገዛዝ ትልቅ ጥቁር ጠባሳ ሆኖ ይመዘገባል።
ዓሊ ላሪጃኒ በኢራን የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ ብርቅዬ ሰው ነበሩ። ከአክራሪዎች ጋር መግባባት የሚችሉ፣ ከምዕራባውያን ጋር የሚደራደሩ እና ወደ መንፈሳዊ መሪው በቀጥታ መድረስ የሚችሉ ሰው ነበሩ።
ጦርነት ተከስቶ የአመራር ክፍተት ሲፈጠርም፣ በራስ-አገዝ ሁኔታ ራሳቸውን የኢራን የስልጣን ማዕከል ላይ አገኙት።
እ.ኤ.አ. በ1958 በኢራቅ ናጃፍ የተወለዱት ላሪጃኒ፣ የሀይማኖት አባት ባይሆኑም በኢራን ውስጥ ካሉ እጅግ ሀያል ከሆኑ የሀይማኖትና የፖለቲካ ቤተሰቦች የወጡ ናቸው። አባታቸው ታላቅ አያቶላህ ሲሆኑ፣ ወንድሞቻቸው ደግሞ በፍትህ እና በተለያዩ የመንግስት ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ ቦታዎችን የያዙ ነበሩ። ቤተሰባቸው "የኢራን ኬኔዲዎች" ተብለው መጠራታቸው በምክንያት ነው።
ይህ የቤተሰብ ዳራ በቴህራን ውስጥ ጥቂቶች ብቻ ያላቸውን እድል ሰጥቷቸዋል፡ ይህም በሀይማኖታዊ ተዋረድ፣ በኢራን አብዮታዊ ዘብ እና በፖለቲካ ልሂቃን መካከል በአንድ ጊዜ ተሰሚነት እንዲኖራቸው አድርጓቸዋል።
ስራቸውን በኢራን-ኢራቅ ጦርነት ወቅት በአብዮታዊ ዘብ ቢጀምሩም፣ በፍጥነት ወደ መንግስት ማእከላዊ መዋቅር ተሸጋገሩ። የባህል ሚኒስትር፣ የሀገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሃላፊ እና ለ12 ዓመታት የፓርላማ አፈ-ጉባኤ ሆነው አገልግለዋል።
በተመሳሳይ ጊዜ፣ በተለያዩ ተፋላሚ ወገኖች መካከል እንደ "ድልድይ" የሚያገለግል ብርቅዬ ግንኙነት መገንባት ችለዋል። ከሁሉም ጋር ተነጋግረው በፖለቲካው ሜዳ መትረፍ ከሚችሉ ጥቂት ሰዎች አንዱ ነበሩ። በብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ሃላፊነት እና በዋና ተደራዳሪነት በነበሩበት ወቅት፣ የኒውክሌር ቀውሱ ማእከላዊ ተዋናይ ነበሩ።
ምንም እንኳን ወግ አጥባቂ ቢሆኑም፣ እ.ኤ.አ. በ2015 ከምዕራባውያን ጋር የተደረገውን የኒውክሌር ስምምነት በኢራን ፓርላማ እንዲጸድቅ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።
ለዓመታት በኢራን ልሂቃን ውስጥ መካከለኛ አቋም እንዳላቸው ይታሰብ ነበር። በድርድር እና በቀውስ አያያዝ የሚያምኑ ሰው ተደርገው ይወሰዱ ነበር።
ነገር ግን እ.ኤ.አ. በ2025 ወደ ደህንነት መዋቅሩ መመለሳቸው እና በተለይም የተከሰተው ጦርነት ማንነታቸውን ቀየረው። በኢራን የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ በሃይል እንዲረታ ትእዛዝ የሰጡት እርሳቸው ሲሆኑ፣ በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ ኢራናውያን ተገድለዋል፣ ሌሎችም ታስረዋል። በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት የዓሊ ካሜኒ መገደልን ተከትሎ፣ ላሪጃኒ ይበልጥ ጠንካራ አቋም በመያዝ "የማይረሳ ትምህርት እንሰጣለን" ሲሉ ዝተው ነበር።
ካሜኒ ከመሞታቸው ጥቂት ቀደም ብሎ፣ ድንገተኛ አደጋ ቢፈጠር ሀገሪቱን እንዲረከቡ በምስጢር የተመረጡ ሰው ነበሩ። ያ አደጋ ሲከሰትም፣ በይፋ ተተኪ ተብለው ባይታወጁም የስልጣን መሪውን የያዙት እርሳቸው ነበሩ።
በተግባር፣ እስላማዊቷ ሪፐብሊክ እጅግ አደገኛ በሆነበት ወቅት "መሪውን የጨበጡ" ሰው ሆነዋል። ዓሊ ላሪጃኒ በኢራን ውስጥ በጣም ታዋቂው መሪ አልነበሩም፤ ነገር ግን ለስርዓቱ እጅግ "አስፈላጊው" ሰው ነበሩ። በውስብስብ የስልጣን መዋቅር ውስጥ ቁርጥራጮቹን ማያያዝ የሚችሉ ፖለቲከኛ ነበሩ።
እርሳቸው መሞታቸው ከተረጋገጠ፣ ቴህራን ያጣችው አንድ ባለስልጣን ብቻ አይደለም፤ የገዛ ስርዓቷን ብልሃት የሚያውቅ የመጨረሻውን "ተርጓሚ" ነው ያጣችው።
ምንጭ፦ ከናፍቴምቦሪኪ ጋዜጣ ከሰፈረ ፅሁፍ ላይ የተወሰደ

3 months ago