በየደረጃው የሚገኙ ተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገልጸ።
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በየደረጃው የሚገኙ ተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል እየተሰራ ያለውን ሥራ በተመለከተ ከክልልና ከተማ መስተዳድር ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ጋር በበይነ መረብ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱም በክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች በሁሉም የክፍል ደረጃ በተለይም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በትምህርት ሚኒስቴር በወረደው ስትራቴጂ መሰረት ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት በስፋት እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።
ከማጠናከሪያ ትምህርት በተጨማሪ ተማሪዎች ከመደበኛ የትምህርት ሰዓት ውጪ ያላቸውን ጊዜ ተጠቅመው እንዲያጠኑ እና ቤተ-መጻህፍትን እንዲጠቀሙ ምቹ ሁኔታዎች በየትምህርት ቤቶቹ መፈጠራቸውን አንስተዋል።
በተለይም ተማሪዎችን በማዘጋጀት ሂደት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በየጊዜው በመፍታትና በቀሩት ቀናት ጉድለቶችን በማሟላትና የተማሪዎችን ዝግጅት በቅርበት በመከታተል ለተማሪዎች ውጤት መሻሻልና ለፈተናው ስኬታማነት በትኩረት እንደሚሰሩ የክልል ቢሮ ሃላፊዎቹ ገልጸዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘም በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ለመምህራንና ለተማሪዎች አጋዥ የሆኑ የትምህርት ይዘቶችንና የመለማመጃ ጥያቄዎችን የያዙ ቪዲዮዎች በድህረ-ገጽ (Portal) ተዘጋጅተው ጥቅም ላይ እንዲውል መደረጉም ተብራርቷል።
atc_news
seledadotio

5 months ago