የመልካም ሰዎች መጉደል ለቤተ ክርስቲያን ነገ ያሳስባል"
- ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
በሀገር ውስጥና በባህር ማዶ በነበረው የወንጌል አገልግሎቱ የሚታወቀው የወጣት መምህር ዘለዓለም ወንድሙ (ወልደ ሰማዕት) የቀብር ሥነ-ሥርዓት በአሁኑ ሰዓት በታላቁ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ ድምቀትና ሐዘን እየተከናወነ ይገኛል።
ከመስቀል አደባባይ የጀመረውና በሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን የታደሙበት ይሄው የሽኝት መርሃ ግብር፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሪዎችና ከፍተኛ የሃይማኖት አባቶች ታጅቦ ቀጥሏል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ በመምህሩ ድንገተኛ ሕልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል። በብፁዕ አቡነ ማቴዎስ አማካኝነት ለታዳሚው በንባብ በተሰማው የቅዱስነታቸው መልእክት ላይ የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ተጠቅሰዋል፦
* መምህር ዘለዓለም በመንፈሳዊ ሕይወቱና በትጋቱ ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ ተስፋ የነበረው፣ ወንጌልን ለማድረስ በገጠርም በከተማም የደከመ አባት መሆኑ ተገልጿል።
* "በምድር ያለው ማደሪያ ቤታችን ቢፈርስም በሰማይ የሰው እጅ ያልሠራው ዘለዓለማዊ ቤት እንዳለን እናውቃለን" (2ቆሮ. 5፡1) የሚለውን ቃለ እግዚአብሔር በመጥቀስ መጽናናትን አስተላልፈዋል።
* ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ውስጥ ሃይማኖትን ወይም ማንነትን መሠረት በማድረግ በቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና ምእመናን ላይ የሚደርሰው ጥቃት ልባቸውን በትካዜ ውስጥ እንደከተተው ሳይጠቅሱ አላለፉም።
መምህር ዘለዓለም ወንድሙ በሰሜን አሜሪካ ለአገልግሎት በሄደበት ወቅት ባጋጠመው ሕመም ከዚህ ዓለም በሥጋ መለየቱ ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠረ ቢሆንም፣ "ያለዋጋ የተቀበለውን የእግዚአብሔር ቃል ለምእመናን በማስተማር አደራውን በሚገባ ተወጥቷል" ሲሉ ቅዱስ ፓትርያርኩ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
በመጨረሻም፣ ሁሉን የሚችል አምላክ ለቤተሰቦቹና ለወዳጆቹ መጽናናትን እንዲሰጥ፣ ለቤተ ክርስቲያንም ተተኪ አገልጋዮችን እንዲያዘጋጅ አባታዊ ጸሎታቸውን አድርገዋል።
"ለአገልጋዩ ወልደ ሰማዕት ነፍስ እረፍተ መንግሥተ ሰማያትን እንመኛለን!"
#eotc

3 months ago