Logo
FIDEL POST NEWS
በኢራን ጥቃት ሳቢያ የኤምሬትስ ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ አገልግሎት አቋረጠ

​በአቡ ዳቢ ብሔራዊ የነዳጅ ኩባንያ (ADNOC) ስር የሚገኘው የሩዋይስ የነዳጅ ማጣሪያ ጣቢያ በደረሰበት የድሮን ጥቃት ምክንያት አገልግሎት ማቋረጡን ሮይተርስ ዘግቧል።

ጥቃቱ በኢራን የተሰነዘረ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በጣቢያው ላይም የእሳት አደጋ አስከትሏል።

​ከኢራን ጋር እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ በፋርስ ባህረ ሰላጤ አካባቢ በቀን 1.9 ሚሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ የማጣራት አቅም መቋረጡን አይ.አይ.አር ኢነርጂ አስታውቋል።
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.