Logo
Getu Temesgen
ከራፕ ማይክ ወደ በትረ ስልጣን
#ethiopia | በሙዚቃው ዓለም "ባሌንድራ ሻሃ" በመባል የሚታወቀው የ35 ዓመቱ ወጣት ራፐር፣ የኔፓልን የመሪነት መንበር ለመረከብ እጅግ ተቃርቧል። ባለፈው ሐሙስ በተካሄደው አገራዊ ምርጫ ድምፅ እየተቆጠረ ባለበት ወቅት፣ ሻሃ ከፍተኛ ድል እንደሚያስመዘግብ ትልቅ ግምት ተሰጥቶታል።

ይህ ስመ-ጥር የራፕ አቀንቃኝ ቀደም ሲል በ2022 በሀገሪቱ ተቀስቅሶ የነበረውን የፀረ-ሙስና አመፅ ተከትሎ፣ የዋና ከተማዋ ካትማንዱ ከንቲባ በመሆን በግል ተወዳድሮ ማሸነፉ ይታወሳል። በከንቲባነት ዘመኑ ለከተማዋ ያበረከተው የላቀ አስተዋፅኦ እና ያመጣው መሻሻል ለአሁኑ የሀገር መሪነት ጉዞው ትልቅ መሰረት ሆኖታል።

በሳምንቱ አጋማሽ በተካሄደው በዚህ ወሳኝ ምርጫ፣ ሻሃ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ኬፒ ሻርማ ኦሊን በራሳቸው የምርጫ ጣቢያ ጭምር በማሸነፍ አስገራሚ ውጤት አስመዝግቧል።

የሲቪል ምህንድስና ተመራቂው ባሌንድራ ሻሃ የሚመራው ፓርቲ በፓርላማው አብላጫ ድምፅ ካገኘ፣ ይህ ወጣት አርቲስት የኤቨረስት ተራራ መገኛ የሆነችውን የደቡብ እስያዊቷን ሀገር ኔፓልን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ለመምራት ታሪክ ይሰራል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #nepalelection #balendrashah #rappertoleader #nepalpolitics #kathmandu #leadership #breakingnews

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.