Logo
YenetaTube
ኢራን ከአሁን በኋላ “አስቀድመው ካላጠቁ” በስተቀር ጎረቤቶቿ ላይ ጥቃት እንደማትፈጸም አስታወቀች

የኢራን ፕሬዝዳንት ማስዑድ ፔዜሽኪያን በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ጥቃት የተፈጸመባቸውን ጎረቤት አገራት ይቅርታ ጠየቁ።
“ጥቃት የደረሰባቸውን አገራት ይቅርታ መጠየቅን አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ” ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።
“ጎረቤት አገራትን የመውረር ሐሳብ የለንም” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ “ሰላም እና መረጋጋትን ለማስፈን” ሲባል ቀጣናዊ ትብብር እንዲኖር ጠይቀዋል።
ፔዜሽኪያን አክለውም የአገሪቱ አመራር ጎረቤቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃትን በተመለከተ ውሳኔ ማሳለፉን ተናግረዋል። የአገሪቱ ጦር ኃይሎች “ከአሁን በኋላ ቀድመው ካላጠቁ በስተቀር ጎረቤት አገራት ላይ ጥቃት እንዳይፈጽሙ” እንደታዘዙ አስታውቀዋል።
“ከአሁን ጀምሮ፣ እነዚያ አገራት ካልተጠቃን በስተቀር ጎረቤት አገራትን ማጥቃት ወይም ሚሳዔል መተኮስ የለባቸውም። ይህንን በዲፕሎማሲ መፍታት አለብን ብዬ አስባለሁ” ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለው ጥቃቶቹ የተፈጸሙት በወታደራዊ አመራሮች መካከል በተፈጠረ የመረጃ ልውውጥ ስህተት ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ ይህ የፕሬዝዳንቱ ንግግር የተላለፈው ኢራን ቅዳሜ ጠዋት ላይ በባህሬን፣ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ከፈጸመች በኋላ እንደሆነ የዜና ወኪሉ አሶሺዬትድ ፕሬስ ዘግቧል።
በተጨማሪም የኢራኑ ፕሬዝዳንት “ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ኢራን ላይ ጥቃት ለመፈጸም እያሰቡ ያሉ [አካላት] የኢምፔሪያሊዝም አሻንጉሊት እንዳይሆኑ” ሲሉ ተናግረዋል። እስራኤል እና አሜሪካን መደገፍ “የክብር እና የነጻነት መንገድ አይደለም” ሲሉም ተደምጠዋል።

BBC

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.