Logo
FIDEL POST NEWS
ትራምፕ ስለ ኢራን የዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ደንታ እንደሌላቸው ገለጹ

​የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ኢራን በዚህ ዓመት በአሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ በሚስተናገደው የዓለም ዋንጫ ላይ ስላላት ተሳትፎ ግድ እንደማይላቸው ገለጹ።

ትራምፕ ለፖሊቲኮ በሰጡት ቃል፣ "ኢራን የተሸነፈች ሀገር ናት፤ በትርፍራፊ ነው የሚኖሩት" በማለት ተሳትፎዋ እንደማያሳስባቸው ተናግረዋል።

​በዚህ ሳምንት በአትላንታ በተካሄደው የፊፋ የቅድመ ዝግጅት ስብሰባ ላይ ሳይገኝ የቀረው ብቸኛ ሀገር ኢራን ብቻ መሆኑ፣ ቡድኑ በውድድሩ ላይ ስለመካፈሉ ጥርጣሬን ፈጥሯል።

ይህ የሆነው በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ከፍተኛ ቀውስ ምክንያት ነው። ኢራን በምድብ ሰባት ከቤልጂየም፣ ግብፅ እና ኒውዚላንድ ጋር የተመደበች ሲሆን፣ ጨዋታዎቿንም በሎስ አንጀለስ እና በሲያትል ከተሞች ለማድረግ ቀጠሮ ተይዞላቸዋል።

ሆኖም ሀገሪቱ በወቅታዊ ፖለቲካዊ ውጥረት ምክንያት በውድድሩ ላይ መገኘቷ አሁንም አጠራጣሪ ሆኗል።
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.