ኦሮሚያ ባንክ የደንበኞች የምስጋና ሳምንት የማስጀመሪያ መርሀ ግብር አካሄደ
ኦሮሚያ ባንክ “ልባዊ ምስጋናችን በተግባር’’ በሚል መሪ ቃል ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የደንበኞች ሳምንት ከዛሬ የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በዋናው መስሪያ ቤት እና በሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች በደማቅ ሁኔታ ማክበር ጀምሯል፡፡
የኦሮሚያ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኦቦ ተፈሪ መኰንን በመርሃ-ግበሩ ማስጀመሪያ ስነ-ሥርዓት ላይ እንደገለጹት ባንኩ ከምስረታው ጀምሮ የደንበኞቹን ፍላጐት ለማርካት፤ ደንበኛ-ተኮር አገልግሎቶችን እያቀረበ 17 ዓመታትን በስኬት እና በዕድገት መጓዙን ገልፀዉ፥ ለዚህም የደንበኞች ሚና የአንበሳዉን ድርሻ ይይዛል ብለዋል።
ደንበኞቻችንን የምንዘክረዉ በአንድ ሳምንት መርሀ ግብር ብቻ ሳይሆን ሁሌም በምንስጠዉ የአገልግሎት ልህቀት እና ፍላጎታቸውን ለማሟላት ባለን ቁርጠኝነትና በትጋት እንደሆነ በንግግራቸዉ አመላክተዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚዉ አክለዉ ባንኩ ዛሬ ለደረሰበት የዕድገት ደረጃ የደንበኞች ሚና የማይተካ በመሆኑ የላቀ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
የኦሮሚያ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር አሰፋ ስሜ በበኩላቸዉ የደንበኞቻችን አብሮነት የዕድገታችን መሰረት በመሆኑ ልባዊ ምስጋናችን እንደሚገባቸው ገልጸው፥ ይበልጥ እናንተን ለማገልገል ቁርጠኛ መሆናችንን ለማረጋገጥ እንወዳለን ብለዋል።
በኦሮሚ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በተካሄደዉ የደንበኞች የምስጋና ሳምንት ማስጀመሪያ መርኃ ግብር ከባንኩ ጋር ለረጅም አመታት በመስራት ዉጤት ያስመዘገቡ ድርጅቶች እና ግለሰቦች እዉቅና እና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል ፡፡
ይህ የደንበኞች የምስጋና ሳምንት በመላው የባንኩ ቅርንጫፎች በልዩ ሁኔታ ይከበራል።

3 months ago