Logo
FIDEL POST NEWS
በኢኳዶር የሚንቀሳቀሱ "ናርኮ-ሽብርተኞችን" ለመምታት የአሜሪካ ጦር ዘመቻ ላይ መሆኑ ተገለፀ

​የአሜሪካ ደቡባዊ እዝ እንደገለጸው፣ የአሜሪካና የኢኳዶር ጦር ኃይሎች በሀገሪቱ በሚንቀሳቀሱ የአደንዛዥ ዕፅ ካርቴሎችና "ሽብርተኛ ድርጅቶች" ላይ የተቀናጀ ወታደራዊ ዘመቻ ጀምረዋል።

ይህ እርምጃ የትራምፕ አስተዳደር በክልሉ የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውርን ለመግታት ከጀመረው ጥረት ጋር የተያያዘ መሆኑ ተነግሯል።

​የደቡባዊ እዝ አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ዶኖቫን የኢኳዶር ጦር ለሚያሳየው ቁርጠኝነት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

በቅርብ ዓመታት ውስጥ ኢኳዶር የኮኬይን ዝውውር ማዕከል በመሆንዋ የጸጥታ ሁኔታዋ እጅግ ተበላሽቷል።

በተለይም በጥር 2024 የታጠቁ ቡድኖች በቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ በፈጸሙት ጥቃት ምክንያት ፕሬዝዳንት ዳንኤል ኖቦአ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸው ይታወሳል።

​አዲሱ ዘመቻ በደቡባዊ ንፍቀ ክበብ የሚደረገውን የሕገ-ወጥ ዕፅ ዝውውር ለመግታት ያለመ ሲሆን፣ ቀደም ሲልም አሜሪካ መሰል እርምጃዎችን በቬንዙዌላና በካሪቢያን ባህር ላይ ስትወስድ ቆይታለች።

አሁንም በኢኳዶር የተጀመረው እርምጃ ቀጠናውን ለማረጋጋት ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.