Logo
Getu Temesgen
ለአሽከርካሪዎችና ለእግረኞች ጥንቃቄ
የዓድዋ ድል በዓልና ዝግ የሚሆኑ መንገዶች
#ethiopia | ​ነገ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም 130ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በፒያሳው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በደመቀ ሁኔታ ይከበራል። በዓሉን በሰላም ለማክበር የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።

​ነገ ከንጋቱ 12:00 ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች፦

​ከቸርችል ጎዳና፦ ባንኮ ዲሮማ መብራት ላይ
​ከአራት ኪሎ፦ ራስ መኮንን ድልድይ ላይ
​ከመነንና የካቲት 12 ሆስፒታል፦ አፍንጮ በር ላይ
​ከእሪ በከንቱ፦ ቀይ ባህር ኮንዶሚኒየም ላይ
​ከአዲሱ ገበያ፦ ሰሜን መብራት ላይ
​ከመርካቶ፦ ደጃዝማች ኃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ ላይ
​ከእንቁላል ፋብሪካ፦ ቅዱስ ዮሐንስ መብራት ላይ

​⚠️ ማሳሰቢያ፦
በእነዚህ መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

​📞 የጥቆማና የመረጃ ስልኮች
​አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በሚከተሉት ነጻ ስልክ መስመሮች ጥቆማ መስጠት ይቻላል፦

👉 990፣ 991፣ 987፣ 816
👉 011-126-43-59 / 011-552-63-02

​#አድዋ130 #የአድዋድል #አዲስአበባ #ትራፊክ #ፖሊስ #ኢትዮጵያ #adwa130 #addisababa #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.