የኢራንን መንፈሳዊ መሪ አሊ ኻሜኒን ለመግደል የሲ.አይ.ኤ እና ሞሳድ ድብቅ ሴራ እንዴት ተሳካ?
ዓለም በሰላም ተኝታ በነበረችበት በዚያ ቅዳሜ ንጋት፣ የኢራን ሰማይ በፈንጂ ድምፅና በብርሃን ነበልባል ተቀደደ። ይህ ተራ ወታደራዊ ግጭት አልነበረም፤ ይልቁንም ለዓመታት ሲታቀድ የቆየ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እና በከፍተኛ የደህንነት መረጃ ብልጫ የተመራ የታሪክ መለወጫ ኩነት ነበር።
የአሜሪካው ሲ.አይ.ኤ እና የእስራኤሉ ሞሳድ የኢራንን መንፈሳዊ መሪ አሊ ኻሜኒን እና የጦር አዛዦቻቸውን በቁጥጥር ስር ለማዋል የተጠቀሙበት ስልት የደህንነት ተቋማቱን ጥብቅ ምስጢር ፍንትው አድርጎ አሳይቷል።
ጥቃቱ መጀመሪያ የታቀደው ለዓርብ ምሽት ነበር። ሆኖም ግን፣ በመጨረሻው ሰዓት ጥቃቱ ወደ ቅዳሜ ንጋት እንዲሸጋገር ተደረገ። የዚህ ውሳኔ ምክንያት የቴክኒክ ብልሽት ሳይሆን "የወርቅ ዕድል" ተብሎ የሚጠራው የደህንነት መረጃ ነበር።
ሲ.አይ.ኤ ከኢራን አገዛዝ የውስጥ ክበብ ባገኘው መረጃ መሰረት፣ አሊ ኻሜኒ እና የኢራን ከፍተኛ የደህንነት ምክር ቤት አባላት በቴህራን እምብርት በሚገኝ አንድ ህንፃ ውስጥ ለድንገተኛ ስብሰባ እንደሚቀመጡ አረጋገጠ።
ይህንን መረጃ ተከትሎ 200 የሚጠጉ የእስራኤል F-15 እና F-35 የጦር ጄቶች ወደ ኢራን ሰማይ ተመዘገዘጉ።
የአየር መከላከያ ስርአቶችን በመጣስ በቀጥታ የኻሜኒ ቢሮ የሚገኝበትን ህንፃ ኢላማ አደረጉ።
ለወራት ሲ.አይ.ኤ እና ሞሳድ የኻሜኒን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ሲከታተሉ ቆይተዋል። ወታደራዊ ተንታኞች እንደሚሉት፣ እንዲህ ያለውን ጥብቅ ጥበቃ የሚደረግለት መሪ በትክክል ባለበት ቦታ ማግኘት የሚቻለው በሳተላይት ብቻ ሳይሆን "በመሬት ላይ ባለ ምንጭ" ነው።
ይህ ማለት በአያቶላዎች አገዛዝ ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን ያላቸው ግለሰቦች መረጃውን ለምዕራባውያን አሳልፈው ሰጥተዋል ማለት ነው። ይህ የተቀናጀ ስራ እንደ ቬንዙዌላው ኒኮላስ ማዱሮ የግዞት ሙከራ ሁሉ፣ በስርአቱ ውስጥ ከፍተኛ መቃቃር እና የደህንነት መላላት መኖሩን ማሳያ ሆኗል።
በጥቃቱ ሳቢያ አሊ ኻሜኒ ብቻ ሳይሆኑ፣ የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ ጀነራል መሐመድ ፓክፑር እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ጀነራል አዚዝ ናሲርዛዴህ መገደላቸው ተረጋግጧል።
በተለይም አድሚራል አሊ ሻምካኒ መገደላቸው ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሯል፤ ምክንያቱም እርሳቸው ኢራን ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በድርድር እንድትመለስ ሲወተውቱ የነበሩ ቁልፍ ሰው ነበሩ።
የአገዛዙ ደጋፊዎች በቴህራን አደባባዮች ቁርአን እየቀሩና እያለቀሱ "በቀል" ሲሉ እየዛቱ ነው።
ደበአንጻሩ አገዛዙ ያሰቃየናል የሚሉ ወጣቶችና ሴቶች በድብቅ ደስታቸውን እየገለጹ ሲሆን፣ የአያቶላዎች ዘመን ማክተሙን እንደ አዲስ ጅማሮ እያዩት ነው።
ሲ.አይ.ኤ ለዋይት ሃውስ ባቀረበው ማስጠንቀቂያ፣ የኻሜኒ ሞት ያስከተለው የፖለቲካ ክፍተት ጉዳዩን ይበልጥ አደገኛ ሊያደርገው እንደሚችል ገልጿል። በስርአቱ ውስጥ የቀሩት ወታደራዊ አዛዦች ስልጣኑን ለመቆጣጠር በሚያደርጉት ጥረት ቀጠናው ወደ ከፋ ጦርነት ሊገባ ይችላል የሚል ስጋት አለ።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጥቃቱን "የሰው ልጅ የሞራል እሴቶችን የጣሰ" ሲሉ ቢኮንኑም፣ እንደ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ፕሬዝዳንት ያሉ መሪዎች ደግሞ "የአምባገነኖች ዘመን ማብቂያ" ሲሉ ገልጸውታል።
የካቲት 21/2018 ዓ.ም በታሪክ መዝገብ ላይ የሚሰፍረው የቴክኖሎጂ እና የደህንነት መረጃ ጥምረት የታላቅ ሀገርን እጣ ፈንታ በሰዓታት ውስጥ የለወጠበት ቀን ሆኖ ነው።አሜሪካንም እንደ አሸባሪ እና የጎበዝ አለቃ የቆጠሩ ብዙ አሉ።
ኢራን አሁን የቆመችው በማይታወቅ ማዕበል መካከል ነው፤ ቀጣዩ መሪ ማን ይሆናል? ጦርነቱስ ወዴት ያመራል? የሚለው የዓለም ቀዳሚ ጥያቄ ሆኗል።

3 months ago