አትሌት ድርቤ ወልተጂ የሁለት ዓመት እገዳ ተጣለባት!
#ethiopia | ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ድርቤ ወልተጂ፣ የዶፒንግ ምርመራ ለማድረግ ፍቃደኛ ባለመሆኗ ምክንያት በስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት (CAS) የሁለት ዓመት እገዳ ተጥሎባታል።
የቅጣቱ ዝርዝር ነጥቦች፦
የቅጣቱ ምክንያት፦ የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን ምርመራ እንዲደረግላት ቢጠይቃትም ፍቃደኛ ባለመሆኗ (Refusal to submit to sample collection)።
የእገዳው ጊዜ፦ ቅጣቱ እስከ 2027 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።
የውጤት መሰረዝ፦ ከየካቲት 2025 ጀምሮ ያስመዘገበቻቸው ውጤቶች በሙሉ ውድቅ ተደርገዋል።
የሜዳሊያ መነጠቅ፦ በ2025 የናንጂንግ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ያገኘችው የብር ሜዳሊያ ተሰርዟል። በዚህም መሰረት ጆርጂያ አዳኝ ቤል የብር፣ ጆርጂያ ግሪፊት ደግሞ የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት እንዲሆኑ ተወስኗል።
አትሌት ድርቤ ነፃ መሆኗን ለማረጋገጥ ጥረት ብታደርግም፣ ምርመራን መቃወም ወይም ፍቃደኛ አለመሆን በአትሌቲክስ ሕግ እንደ አዎንታዊ (Positive) ውጤት ስለሚቆጠር ቅጣቱ ሊጸናባት ችሏል። በዚህም ምክንያት በ2025 የቶኪዮ ዓለም ሻምፒዮና ላይ እንዳትሳተፍ መደረጓ ይታወሳል።
✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ (ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)
#diribewelteji #athleticsethiopia #dopingban #cas #worldathletics #antidoping #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

3 months ago