Logo
YenetaTube
"ለሰላም ዕድል እንስጥ!" — ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም ገብረኢየሱስ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያና በቀጠናው ባሉ የተለያዩ ቋንቋዎች ባስተላለፉት መልዕክት የጦርነትን አውዳሚነት በማውገዝ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብና የሚመለከታቸው አካላት ወደ ሰላም መንገድ እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።

"ጦርነት ትርፉ ሞትና ጥፋት ነው"
ዶ/ር ቴዎድሮስ በመልዕክታቸው ጦርነት ከመቼውም ጊዜ በላይ ለሰው ልጆች ስቃይ፣ለረሃብና ለከፍተኛ መፈናቀል መንስኤ መሆኑን አስታውሰዋል።

ጦርነት በሰው ልጅ ጤናና በሕይወት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ እጅግ የከፋ መሆኑን በመጥቀስ "ለሰላም ዕድል እንስጥ!" ሲሉ ተማጽነዋል።

እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ ፖለቲካዊ መፍትሄዎች ሁልጊዜም ቢሆን አሉ ሆኖም እነዚህን መፍትሄዎች ተግባራዊ ለማድረግ "እውነተኛ ጀግንነት" እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። እውነተኛ ጀግኖች ሰላምን ይመርጣሉ ለሰላም ዕድል እንስጥ" በማለትም ሰላም የሰው ልጅ ቀዳሚ ፍላጎት መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ በመልዕክታቸው ማጠቃለያ ላይ "ሰላም ከሁሉ የተሻለ መድኃኒት ነው" (Peace is the best medicine) በማለት የጤና ባለሙያነታቸውንና የዓለም ጤና ድርጅት መሪነታቸውን ባሳየ መልኩ ሰላምን ከጤና ጋር አስተሳስረው ገልጸውታል።

ይህ የዶ/ር ቴዎድሮስ ጥሪ የቀረበው በመቐለና በተለያዩ አካባቢዎች ያለው ሰብአዊ ቀውስና በአሜሪካና በኢራን መካከል ያለው ወታደራዊ ውጥረት በከረረበት ወቅት መሆኑ ጉዳዩን ይበልጥ ትኩረት የሚሻ ያደርገዋል።

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.