የካፒታል ገበያ እና መዋለ ንዋይ ሰነድ
በኢትዮጵያ ህግ ማእቀፍ
የኢትዮጲያ ካፒታል አዋጅ ቁጥር 1248/13
ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው
መግቢያ #ethiopia | የካፒታል ገበያ በኢትዮጵያ በህግ ማእቀፍ ተደግፎ የመዋለ ሰነዶችን ሽያጭ በማሳደግ ረገድ ሀገራችን የካፒታል አዋጅ ቁጥር 1248/13 አውጥቶ በስራ ላይ መዋሉ የእነዚህ ሰነዶችን ሽያጭ ገበያ በመፍጠር ኢንቨስተሮችን ከመሳብ ፣ የንግድ ማህበራትን፣ባንኮችን ከማሳደግ፣ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት ከፍ ከማድረግ አንጻር ዘርፈ ብዙ የተሳለጠ የንግድ ትስስር የሚፈጥር ሲሆን በዚህ ጽሁፍ ከህግ ጋር ተያይዞ ያለውን ይዘት ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ለመስጠት ይህን ጽሁፍ ወደ እናንተ አቅርበናል።
1. የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ታሪካዊ ዳራ
ኢትዮጵያ ብዙ የህግ ታሪክ ስለ ካፒታል ገበያ እንደሌሎች ሀገራት እንደሌላት የተለያዩ ስለካፒታል ገበያ የተመለከቱ የኢትዮጵያን ታሪክ መመልከት የሚቻል ነው። የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ታሪካዊ ዳራን ስናጤን በአጼ ዘመነ መንግስት እ.ኤ.አ በ1867 ዓ.ም በአጼ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት የኢትዮ ጅቡቲን ሀዲድ ለመዘርጋት የ40 ሚሊዮን ፍራንክ አክስዮን በፈረንሳይ ሀገር መሸጣቸው ታሪክ ያወሳል።በእሳቸው ዘመን የተቋቋመው የመጀመርያው ባንክ፣ አቢሲኒያ ባንክ ሲመሠረት አክሲዮኖቹ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ኒውዮርክ፣ ፓሪስ፣ ለንደንና ቪየና እንደተሸጡ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡
እ.ኤ.አ. በ1956 የኢትዮጵያ የቄራዎች ድርጅት ለሕዝብ ሽያጭ የወጣ ሲሆን፣ እሱን ተከትሎ እ.ኤ.አ. ከ1957 እስከ 1963 ባለው ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ ጠርሙስ ፋብሪካ (Ethiopian Bottling Company)፣ ኢንዶ-ኢትዮጵያን ጨርቃ ጨርቅ፣ ኤችቪኤ ኢትዮጵያ፣ ሳባ ጠጅ፣ ተንዳሆ ተክልና የአዲስ አበባ ባንክ ለሕዝብ ሽያጭ መውጣታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተጨማሪ እ.ኤ.አ. በ1959 ወንጂ ስኳር ፋብሪካ ለሕዝብ ሽያጭ የቀረበ ድርጅት መሆኑንና በወቅቱ በሦስት ወራት ውስጥ ከአክሲዮን ሽያጭ 2.5 ሚሊዮን ዶላር መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን፣ ኤችቪኤ የተባለው የሆላንድ ኩባንያ አብዛኛውን አክሲዮን መግዛቱ ይነገራል፡፡ እንዲሁም ሕዝቡም ቀላል ሊባል በማይችል መልኩ በግብይት መሳተፉንና ድርሻ መግዛቱን ጄዲቮን ፒስኬ የተባለ ጸሐፊ፣ «አክሲዮንና የአክሲዮን ግብይት በአዲስ አበባ» በሚለው መጽሐፉ ከትቦት ይገኛል።
በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በ1960 ዓ.ም. በኢትዮጵያ መንግሥት ባንክ (State Bank of Ethiopia) ውስጥ የአክሲዮን ግብይት መምርያ መቋቋሙ የአክሲዮን ግብይቱን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡ ይህንን መምርያ ማደራጀት የአክሲዮን ገበያን ለማስፋፋት በመንግሥት የተወሰደ የመጀመርያው ተቋማዊ አደረጃጀት ዕርምጃ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በወቅቱ የተለያዩ ኢንቨስተሮችን በግብይት በማሳተፍና ዋጋ እንዲሰጡ በማድረግ፣ እንዲሁም በተለያዩ መንገዶች ዋጋ እንዲወሰን ይደረግ ነበር፡፡
እ.ኤ.አ. በ1965 የአክሲዮን ግብይት እያደገ በመሄዱ፣ የሕዝብን እምነት በማግኘቱ፣ ኢኮኖሚውም ዕድገት በማሳየቱ፣ አዳዲስ ኀይለስላሴ ዘመነመንግስት የካፒታል ገበያ የህግ ማእቀፍ ኖሮት የተለያዩ አስፈጻሚ ተቋሟት የማቋቋም የማደራጀት እና የመነቃቃት ስራዎች ተሞክረዋል። ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለመገንባት በተደረገው ህዝባዊ ንቅናቄም ብዙ የቦንድ ሽያጭ ለዜጎች፣ ሀገር በቀል ድርጅቶች ፣ ለትውልደ ኢትዮጲያን ፣ ዲያስፖራ ለሌሎችም ተሳታፊ አካላት ተሽጦ በብዙ ቢሊዮን ብር ተሰብስቦ ታላቁን ህዳሴ ግድብ ተገንብቷል።
ይህ ህጉ ከመውጣቱ በፊት ባልተማከለ አሰራር የተፈጸመ ቢሆንም የካፒታል ገበያ ስረአት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል። ከዚህም ባለፈ የገበያ መር ስረአት የሚደግፍ ሲሆን ለነጋዴዎች፣ለባለሀብቶች፣ ለሀገር እድገት መንሰራራት፣ለአለምአቀፍ የገበያ ትስስር፣ለዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ፣ለአጠቃላይ የገበያ እድገት እንቅስቃሴ ከፍተኛ በርን የከፈተ ሲሆን እኝህን መሪዎችንና እና ተባባሪዎቻቸውን አለማመስገን ንፉግነት መሆኑ ያነበበኩት እና ለመመረቂያ ጽሁፌ ያጠናውት " The Challenges and Opportunities of the capital market proclamation implementation " ማለትም በአማረኛ ለማስገንዘብ ያህል "የካፒታል ገበያ አዋጅ አፈጻጸም ተግዳሮት እና መጻኢ እድል" በሚል በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ የታተመው ጹሁፍ ምስክር ይሆኑኛል።
ይሁን እንጂ የደርግ መንግስት ስልጣን ከያዘ በኋላ የሶሻሊስት ስረአት መንግስትን ባህርይ ያለው መሆኑን ተከትሎ የካፒታል ገበያ የህግ ማእቀፍ እንዳይኖረው እንዲሁም የገበያ መር ስረአትን የማይከተል በመሆኑ የካፒታል ገበያ ቦታ እንዳይኖረው አድርጎት አሁን ግን ጊዜው ደርስ የህግ ማእቀፍ እንዲኖረው ተደርጓል።
2. አሁን ላይ የካፒታል ገበያ የህግ ማእቀፍ ምን ይመስላል?
አሁን ባለንበት የኢፊድሪ ህገመንግስት ዲሞክርያሲያዊ እና ገበያ መር ስረአትን ፈቃጅ ሲሆን ይህን ተከትሎም ለሀገር እድገት የሚበጁ የንግድ ስረአታችንን የሚያዘምኑ ከአለም የገበያ ስረአት ጋር እኩል የሚሄዱ ህጎች እየወጡ የሚገኙ ሲሆን አንዱም የኢትዮጲያ ካፒታል ገበያ አዋጅ ቀጥር 1248/13 ነው።በዚህ አዋጅ አንቀጽ 3 ላይ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የተቋቋመ ሲሆን ይህን ተከትሎም የተለያዩ ደንብ እና መመሪያዎች በመውጣት ላይም ይገኛሉ።
ይህ ለሀገራችን እድገት እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ሌሎች ህጎችም ሊደግፉ እና ተጣጥመው ሊተገበሩ የሚገባ በመሆኑ የብሔራዊ ባንክ አዋጅ፣የንግድ ባንክ አዋጅ፣ የኢፊድሪ ንግድ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 ሌሎች የፋይናንስ እና የንግድ ተቋማት ህጎች በመውጣት በመሻሻል ላይ ይገኛሉ። በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/13 ስር የሚታቀፉ ወይም የታቀፉ ዘርፈ ብዙ ተቋማት የሚገኙ ሲሆኑ ዋናው ጉዳይ ግን የሙአለ ንዋይ ሰነድ ገበያን ተፈጻሚ የሚያደርጉ ናቸው።
የሙአለ ሰነድ ገበያ በዋናነት ለመጥቀስ ያህል በአዋጁ አንቀጽ 31 መሠረት የሚመሰረት ሲሆን ይህን በተመለከተ የኢፊድሪ መንግስትም ስራ መጀመሩን አብስሯል። ይህ ዋናው የአዋጁ መቋቋም መሠረታዊ አላማ ነው። ሌላው የመወእለ ሰነዶች አስቀማጭ ክፍያ አጣሪ ፈጻሚ ኩባንያ በአዋጁ የህግ እውቅና የተሰጠው ሲሆን ይህ ግብይት የሚፈጸምባቸውን ሰነዶች ክፍያ አፈጻጸም ከእዳና ከተለያዩ ክፍያዎች ነጻ ስለመሆኑ በማጣራት ሰነዶችን በመለየት የሚያስቀምጥ ነው። በዚህ ረገድ ብሔራዊ ባንክም ስልጣን የተሰጠበት አግባብ በአዋጁ ላይ ተዘርዝሮ የተቀመጠ ነው። የመንግስት መዋአለ ሰነዶችን በተመለከተ ሰነዶችን የማስቀመጥ የማስተዳደር ስልጣን ተሰጥቶታል።
3. .ሙአለ ንዋይ ሰነዶች ምንድን ናቸው?
የሰነደ ሙዓለ ንዋይ (Securities) ማለት በገንዘብ ሊተመን የሚችል ባለቤትነትን የሚገልጽ ሰነድ ማለት ሲሆን ሊሸጥ፣ ሊለወጥ ወይም በዋስትና ሊሰጥ የሚችል መብት የሚያቋቁም ሰነድ ነው፡፡ በእኛ አገር የሚታወቁት የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ዓይነቶች አክሲዮን፣ ቦንድና የግምጃ ቤት ሰነድ ናቸው፡፡ ባደጉት አገሮች የተለያዩ ዓይነት የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ይገበያያሉ፡፡ እነዚህም አክሲዮኖችን (Shares)፣ የዕዳ ሰነዶችን (Debt Instruments)፣ ብድሮችን (Loans)፣ ቦንዶችንና ሌሎች ወደ ኩባንያ ካፒታልነት ሊቀየሩ የሚችሉ ስምምነቶችን ያካትታል፡፡ በተጨማሪም ሁሉም በመንግሥት ወይም በመንግሥት የልማት ድርጅቶች የወጡና
ለግብይት የሚውሉ የሕዝብ የብድር ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን፣ ለወደፊት የሚፈጸሙ የውል ዓይነቶችን (Futures)፣ ያለ ግዴታ የመግዛት ወይም የመሸጥ መብት ለገዥው የሚሰጡ ሰነዶችን (Options)፣ ተዛማጅን (Derivatives) እና በጋራ የኢንቨስትመንት ፈንድ ውስጥ ያለ የድርሻ ክፍልፋይ (Units in a Collective Investment Scheme) ይይዛል፡፡
እነዚህንና ሌሎች የካፒታል ገበያ ሰነዶችን በአገራችን በተማከለ ገበያ ለማገበያየት እንዲያመች እንደ ሌሎቹ አገሮች የራሱ የሆነ ሒደትን መዘርጋት፣ መደገፍ፣ መቆጣጠር ብሎም መከታተል የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የካፒታል ገበያ አዋጅ ወጥቶ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/13 አንቀጽ 2(62) መሠረት ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ማለት ከላይ በሌሎች አገሮች ግብይት ይደረግባቸዋል የተባሉትን ሰነዶች ጨምሮ፣ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ናቸው ብሎ የሚወስናቸውን ማናቸውም በግብይት የድርሻ ባለቤትነትን የሚያረጋግጡና በባለሥልጣኑ ፈቃድ መሠረት የሚተላለፉ ሰነዶችን ይጨምራል፡፡
4. የሙአለ ሰነዶች ገበያ መመዝገብ እና መሠረዝ
ሌላው ደግሞ በዚህ መግቢያ መነሳት ያለበት ነጥብ በሙአለ ሰነዶች ገበያ የሚመዘገቡ ሰነዶች ሲሆኑ በዚህ የሚሳተፉ ተቋማት አስፈላጊውን መሥፈርት አሟልተው በጥንቃቄ ተመርምረው የሚመዘገቡ ናቸው። እነዚህም የተመዘገቡ ኩባንያዎች listing companies ሲባሉ ነገር ግን በተለያየ ምክንያት በግብይት ሂደት ውስጥ መረጃ በማሳሳት ገብተው ወይም ወንጀል ፈጽመው ወይም ግዴታቸውን ሳይወጡ ቀርተው እንደሆነ ከገበያው የሚሰረዙበት ስረአት በህጉ የተቀመጡ ሲሆን ከገበያው የተሰረዙ ኩባንያዎች/delisting campany/በመባል ይታወቃሉ። እነዚህን የካፒታል ገበያ አላማ ከዳር ለማድረስ መንግስት በራሱ ብቻ የሚከውነው ሳይሆን ለተለያዩ አገልግሎት ብቁ ለሆኑ የግል አግልግሎት ሰጪዎች ብቁ ሆነው ከተገኙ ፍቃድ በሚሰጥበት አግባብ የሚጠበቅባቸውን መስፈርት የሚያሟሉ ከሆነ ፍቃድ ተሰጥቶአቸው የሚሰሩበት አግባብ እንዳለ በአዋጁ አንቀጹ 55 ላይ በዝርዝር ተቀምጧል።
5. የኢትዮጲያ ካፒታል ገበያ አስተዳደር ፍርድ ቤት
ሌላው ትኩረት የምናደርግበት በአዋጁ አንቀጽ 64 መሠረት የተቋቋመ ሲሆን ይህም የካፒታል ገበያ አስተዳደር ፍርድ ቤት ነው። ይህ ፍርድ ቤት ሙእለ ሰነዶች ግብይት ላይ አስመልክቶ በዚህ አዋጅ ሽፋን ስር በሚወድቁ አጠቃላይ ተግባራት ላይ በባለስልጣኑ ውሳኔዎች ላይ በሚሰጡ በሚተላለፉ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ላይ ቅሬታ ያለው ወገን ክስ አቅርቦ የሚታይበት ሲሆን በዚህ ፍርድ ቤት የሚሰጡ ውሳኔች ላይ ቅር የተሰኘ ወገን በመሠረታዊ የህግ ስህተት ላይ ብቻ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ የሚጠየቅበት ይሆናል። ይህ ማለት የፍሬ ነገር ክርክር ጉዳዮች በተመለከተ የክርክር ሂደት እዚሁ የካፒታል አስተዳደር ፍርድ ቤት የሚያልቅ በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግ የሚገባው ነው።
በዚህ ካፒታል ገበያ አስተዳደር ፍርድ ቤት የሚሾሙ ዳኞች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲሆን በዚህ ዘርፍ የተለየ በእውቀት በልምድ በስልጠና በሀገር ወጭም ጭምር የዳበሩ ልዩ እውቀትና ልምድ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል። ይህ ካልሆነ ከፈጣን እና ፍትሀዊ አገልግሎት ከመስጠት አንጻር በቶሎ ውሳኔ የማይሰጥበት ከሆነ በዚህ ዘርፍ ለሚሳተፉ ኢንቨስተሮች፣ተቋማት ለሙአለ ሰነድ ግብይት ስራ ዘርፍ እና ኢትዮጲያ ሀገራችን ለጀመረችው የዚህ የካፒታል ገበያ እድገት ጎታች ሊሆን ስለሚችል ይህ ኢንቨስተሮችን የሚያርቅ ተስፋ የሚያስቆርጥ ይልቁንም የማይስተማምን ተገማችነትን የሚያሳጣ መሆን የለበትም ። ከዚህ አንጻር የፍርድ ቤቱ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች፣በወንጀል ጉዳይ ደግሞ መርማሪዎች፣አቃቢ ህጎች በተለየ እውቀት ፣ ልምድ፣ ስልጠና የዳበሩ ሊሆኑ ያስፈልጋል። ይህም ማለት ዳኞችን በዋናነት ጨምሮ ስለ ሙአለ ንዋይ ሰነዶ ምንነት፣ባህርይ፣ግብይት፣ ህግና መመሪያዎቻቸውን በዚህ ዘርፍ የሚሳተፋትን ኩባንያ፣ኢንቨስተሮችን፣ፍቃድ የተሰጣቸውን አገልግሎት ተቋማትን በተሳታፊ ኩባንያ ውስጥ ያሉ ሰራተኞች መብትና ግዴታዎችን የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ስልጣኑንና ተግባሩን ኀላፊነቱን ተጠያቂነቱን በዚህ ዘርፍ ስር የሚገኙ ሰራተኞችን መብት ግዴታ አሰራሮቻቸውን ማወቁ ለዚህ ለሚመለከተው ፍርድ ቤት ፍትህ አሰጣጥ እጅግ ጠቃሚ ነው።
6. ሲጠቃለል
ይህን አዋጅ ባቀፈው ህግጋት እና አላማ ልክ ተፈጻሚ ለማድረግ ያሉን መልካም አጋጣሚዎች እንደ ሀገር ምን ምን እንደሆኑ መታየቱ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። የዚህን አዋጅ ተፈጻሚነት ከዳር ከማድረስ አንጻር በሚደረገው ከፍተኛ ትንቅንቅ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮች ምን ምን ናቸው ለእነዚህስ መሠረታዊ የሚሆን መፍቴዎች ምንድን ናቸው በሚሉ በዝርዝር አስፈላጊ በሚባሉ ነጥቦች ላይ መሠረታዊ ትንተና ሊሰጥበት የሚገባ ሲሆን የሌሎች ሀገረች ልምድና ተሞክሮ ጭምር የመፍትሄ አካል ሆኖ መወሰዱ ወሳኝ ነገር ነው።
በአጠቃላይ የካፒታል ገበያ ህግ ለሀገራችን እጅግ ጠቃሚ ከመሆነ የተነሳ ከ19ኛ ክ/ዘመን ወዲህ ጀምሮ ባለተማከለ የገበያ አሰራር የሙአለ ሰነድ ሽያጮች ይከናወኑ እንደነበሩ እና በዚህ ለሀገራችን እድገት ወሰኝ የነበረ ሲሆን ይህንና አለምአቀፍ ልምዶች ህጎች ትስስሮች በመረዳት በተማከለ የካፒታል ገበያ ስረአት ውስጥ በመጓዝ ሀገርን እና ዜጎችን በኢኮኖሚ እድገት ከፍ ለማድረግ የካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/13 ይህንንም ተከትሎ ሌሎች ሊያሰሩ የሚችሉ ደንቦችን መመሪያዎችን በማውጣት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከዚህ በፊት የነበሩ የንግድ የባንክ፣የፋይናንስ ህጎች በመሻሻል ላይ ይገኛሉ።
መንግስትም ይህን የሚመጥን በህግ ማእቀፉ እንደተቀመጠው በቴክኖሎጂ የታገዙ ተቋማትን መገንባት የሚገባ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሰው ሀይል ማብቃትም በተመለከተ ትኩረት ሊወሰድበት የሚገባው ነው። ማህበረሰቡ ኢንቨስተሩ ኩባንያውም በዚህ ልክ እንዲነቃቃ አስፈላጊውን ግንዛቤ ሊሰጠው ያስፈልጋል። የካፒታል ገበያ ባለስልጣኑም በአዋጁ የተሰጠውን ትልቅ ኀላፊነት ለመወጣት አስፈላጊውን ዝግጅት ሊወስድ የሚገባ ሲሆን በግብይት ሂደት ተሳታፊ የሆኑ ቅን ባለሀብቶችን መብት ጥበቃ ሊያደርግ የሚያስፈልግ ሲሆን አጭበርባሪዎችን ለአሰራር እንቅፋት የሚፈጥሩትን በመለየት እንዲታረሙ ከማድረግ አንጻር ተገቢውን ጥረት ሊያደርግ የሚገባው ነው። ይህ ሲሆን የካፒታል ገበያ አዋጅ 1248/13 ተፈጻሚ በማድረግ ለሀገራችን ትልቅ የኢኮኖሚ ፋይዳ ያለው ስለመሆኑ አያጠያይቅም።
ማጣቀሻዎች/References/
1. የኢፊድሪ ህገመንግስት አዋጅ ቁጥር 1/1987
2. የካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/13
3. Fantahun Delelew, Challenge and opportunities of the implementation of capital proclamation 1248/13,Addisababa University
(የካፒታል አዋጁ አፈጻጸም ተግዳሮት እና መጻኢ እድል)
4. የብሔራዊ ባንክ አዋጅ ቁጥር 1359/17
5. ስለ ባንክ ስራዎች አዋጅ ቁጥር 1360/17
https://www.facebook.com
https://t.me/Fantahunlawye...

3 months ago