Logo
YenetaTube
“ቪዥን የጤና አገልግሎት በአፍሪካ መድረክ በከፍተኛው የዳይመንድ ደረጃ ተሸለመ”

በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት ላለፉት 15 ዓመታት በትጋት ሲሰራ የቆየው ቪዥን የጤና አገልግሎት (VHC) በታዋቂው ግራንድ አፍሪካን (Grand African) የተቋማት ሽልማት ከፍተኛው ክብር የሆነውን የዳይመንድ ደረጃ (Diamond Level) ዋንጫ ተቀዳጅቷል።

ተቋሙ ይህንን ታላቅ ሽልማት ሊያገኝ የቻለው ለታካሚዎች በሚሰጠው ልዩ ትኩረት እና እንክብካቤ ለአገልግሎት ጥራት እና ለደህንነት ባለው ጽኑ አቋም እንዲሁም ባለፉት 15 ዓመታት ባሳየው ተከታታይ እና አስተማማኝ እድገት መሆኑ ተገልጿል።

የተቋሙ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ስምዖን ሃብተአብ እንደገለጹት ቪዥን የጤና አገልግሎት ስራውን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ሲስተም (Digital Healthcare) በመደገፍ ረገድ ግንባር ቀደም ነው። ይህም የታካሚዎችን መረጃ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመያዝ የምርመራ ውጤቶችን ለማፍጠን እና የታካሚዎችን የጥበቃ ጊዜ በእጅጉ ለመቀነስ አስችሏል።

ተቋሙ በአሁኑ ወቅት ከ70 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ከመፍጠሩም በላይ፣ በበጎ አድራጎት ስራዎች ንቁ ተሳትፎ ያደርጋል። የድርጅቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ ኮ/ል አማዘ አብርሀ እንደገለጹት አቅም ለሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የዋጋ ቅናሽ በማድረግ እና የተለያዩ ድጋፎችን በመስጠት የዜጎችን ህይወት በመታደግ ላይ ይገኛል።

የወደፊት ራዕይ የቴክኖሎጂ ሽግግር
ቪዥን የጤና አገልግሎት በቀጣይነት አገልግሎቱን ይበልጥ ለማዘመን የሚከተሉትን እቅዶች ይዞ እየሰራ ይገኛል፦

* የተቀናጀ የቴሌ-መድኃኒት (Tele-medicine) ኔትወርክ መዘርጋት፣
* በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የታገዙ የህክምና ውሳኔ መስጫ ስርዓቶችን መተግበር፣
* ተንቀሳቃሽ የህክምና አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን (Mobile Units) ማዘጋጀት፣
* የዲጂታል ጤና እና የምርመራ አካዳሚ በማቋቋም የዘርፉን እውቀት ማሳደግ ይገኝበታል

እ.ኤ.አ. በ2011 በዶ/ር ስምዖን ሃብተአብ የተመሰረተው ቪዥን የጤና አገልግሎት (VHC) ዋና መቀመጫውን አዲስ አበባ በማድረግ ክሊኒካዊ የፋርማሲ፣ የማማከር፣ የላብራቶሪ እና የዲያግኖስቲክ ህክምናዎችን በላቀ ጥራት በመስጠት ላይ ይገኛል።

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.