የአሜሪካ ጦር በካሪቢያን ባህር ላይ በፈጸመው ጥቃት 3 ሰዎች ተገደሉ!
የአሜሪካ ደቡባዊ እዝ (SOUTHCOM) በካሪቢያን ባህር ላይ የዕፅ ዝውውር በሚያከናውን ጀልባ ላይ "ገዳይ ጥቃት" መፈጸሙን አስታወቀ።
ጥቃቱ የተፈጸመው "ኦፕሬሽን ሳውዘርን ስፒር" (Operation Southern Spear) በሚል በሚንቀሳቀሰው ግብረ ሃይል ሲሆን፣ ትዕዛዙን ያስተላለፉት አዲሱ የደቡባዊ እዝ አዛዥ ጀነራል ፍራንሲስ ኤል ዶኖቫን ናቸው ሲሉ በርካታ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃነን ዘግበዋል።
በጀልባዋ ላይ የነበሩ 3 "ናርኮ-አሸባሪዎች" ናቸው የተባሉ መገደላቸው የተነገረ ሲሆን በአሜሪካ ወታደሮች ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል።
ጀልባዋ በአሸባሪ ድርጅቶች የምትመራ እና ከፍተኛ መጠን ያለው ዕፅ ጭና በህገ-ወጥ መስመር ላይ ስትጓዝ እንደነበር የስለላ መረጃዎች ማረጋገጣቸውን እዙ ገልጿል።
ይህ ጥቃት የትራምፕ አስተዳደር በላቲን አሜሪካ የዕፅ አዘዋዋሪዎችን ለመደምሰስ የጀመረው መጠነ ሰፊ ወታደራዊ እርምጃ አካል ነው ።
ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ እስካሁን በተፈጸሙ ተመሳሳይ 38 ጥቃቶች የሟቾች ቁጥር 133 ደርሷል።

4 months ago