Logo
Getu Temesgen
"አፍሪካን መበዝበዝ ይብቃ!"
#ethiopia | የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ አፍሪካ በአለም አቀፍ መድረክ የሚገባትን ቦታ እንድታገኝ እና ሀብቷ ለገዛ ህዝቦቿ እንዲተርፍ ጥሪ አቅርበዋል። ዋና ጸሐፊው "ዝርፊያ እና ብዝበዛ ይብቃ፤ የአፍሪካ ህዝብ ከአፍሪካ የተፈጥሮ ሀብት ተጠቃሚ መሆን አለበት" ሲሉ ተደምጠዋል።

ዋና ዋና የንግግሩ ነጥቦች፦

* የአለም አቀፍ ተቋማት ሪፎርም፦ "ይህ 2026 እንጂ 1946 አይደለም" ያሉት ጉቴሬዝ፣ አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ተገቢው ውክልና ሊኖራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

* ኢኮኖሚ እና ዕዳ፦ የአፍሪካ ሀገራት ከሚያገኙት እርዳታ ይልቅ ለዕዳ ክፍያ እና በህገ-ወጥ መንገድ ለሚወጣ ገንዘብ የሚያጡት ይበልጣል ብለዋል። የአለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓቱ እንዲሻሻል እና የአፍሪካ የብድር ወጪ እንዲቀንስም ጠይቀዋል።

* የአየር ንብረት ለውጥ፦ አፍሪካ 60% የሚሆነውን የአለም የፀሐይ ኃይል አማራጭ ይዛ፣ የምታገኘው የኢንቨስትመንት ድርሻ ግን 2% ብቻ መሆኑን በመጥቀስ፤ በበለጸጉ ሀገራት በኩል የሚደረገው የአየር ንብረት ድጋፍ (Adaptation Finance) በሦስት እጥፍ እንዲያድግ ጥሪ አቅርበዋል።

* ሰላምና ደህንነት፦ በሱዳን አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ በደቡብ ሱዳን ፖለቲካዊ ውይይቶች እንዲቀጥሉ እና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሀገር ሉዓላዊነት እንዲከበር አሳስበዋል።

ሌሎች የጉባኤው ኩነቶች፦

* አዲስ ሊቀመንበር፦ የአፍሪካ ህብረት የ2026 የሊቀመንበርነት ተረኛ ተረካቢ ቡሩንዲ ሆናለች። የ2025 ሊቀመንበር የነበሩት የአንጎላው ፕሬዝዳንት ጆአዎ ሎሬንሶ ኃላፊነታቸውን አስረክበዋል።

* የውኃ እና ሳኒቴሽን ጉዳይ፦ የዘንድሮው የህብረቱ ጭብጥ "ዘላቂ የውኃ አቅርቦት እና የሳኒቴሽን ሥርዓትን ማረጋገጥ" የሚል ሲሆን፣ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ሌሎች መሪዎች ሪፖርቶችን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

* ቅኝ አገዛዝ፦ መሪዎቹ ቅኝ አገዛዝን "በሰው ልጅ ላይ የተፈጸመ ወንጀል" (Crime against humanity) ተብሎ እንዲፈረጅ በሚቀርብ ጥናት ላይ ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ለ Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) ሚዲያና ኮሙኒኬሽንስ
ያፌት ገ/ህወት
ከአፍሪካ ኅብረት
አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ
#un #guterres #africanunion #ausummit2026 #addisababa #africa #nomoreexploitation #climatejustice #ethiopia #sudan #somalia

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.