ለሰርጉ እየተዘጋጀ የነበረው ወጣት ቴዎድሮስ አዲሱ ሞሲሳ አሳዛኝ እረፍት
#fastmereja I የጋብቻ ስነ ስርዓቱን ለመፈጸም አንድ ወር ብቻ ቀርቶት የነበረው ወጣት ቴዎድሮስ አዲሱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።
የነቀምቴ ከተማ ተወላጅ ነው። የመሠረታዊ ትምህርቱን በነቀምቴ ካቶሊክ ኪዳነ ምህረት ትምህርት ቤት፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በነቀምቴ ትምህርት ቤት አጠናቆ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገብቷል።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ለበርካታ ዓመታት Ground Technician የአውሮፕላን ጥገና እና ደህንነት ቁጥጥር ላይ ሲሰራ ቆይቷል።
ከጥቂት ዓመታት በፊት ወደ ካናዳ በማቅናት እዚያው በሙያው እያገለገለ ይገኝ ነበር። ቴዎድሮስ በወጣትነት ዕድሜው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ ሲሆን፣ አስከሬኑ ዛሬ ወደ ትውልድ ከተማው ነቀምቴ እየሄደ መሆኑ ተገልጿል።
ፈጣሪ ለነፍሱ ምህረትን ይስጥ፤ ለቤተሰቦቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን። 💔

4 months ago