Logo
FastMereja
“ብስክሌት በአዲስ" ወርሃዊ የብስክሌት ፌስቲቫል የፊታችን እሁድ ይካሄዳል!
#fastmereja : ነፍ ኮምዩኒኬሽን እና ኤቨንት ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፣ በአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን እና በአዲስ አበባ ወጣትና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር "ብስክሌትን በአዲስ" በሚል መሪ ቃል የብስክሌት ፌስቲቫል የፊታችን እሁድ የካቲት 1/2018ዓ.ም ሊካሄድ መሆኑ ተገልጿል።

ፌስቲቫሉ የፊታችን እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ ረፋዱ 5:00 ድረስ በአራዳ ፓርክ እንደሚከናወን ተገልጿል።

ፌስቲቫሉ ለሁሉም ዕድሜ ከፍሎች ክፍት ሲሆን ተሳታፊዎች በነፃ መካፈል እንደሚችሉ ተገልፆ ብስክሌት ያለው ይዞ መምጣት የሚችል ሲሆን የሌለውም በተዘጋጀው ብስክሌት መሳተፍ እንደሚችልም ነዉ የተገለፀዉ።

ከዚህ ቀደም አምስት ጊዜያት በመዲናችን አዲስአበባ" ብስክሌት በአዲስ" መሪ ቃል ወርሃዊ የብስከሌት ፌስቲቫል በየወሩ የመጨረሻ እሁድ ሲካሄድ መቆየቱም ተገልጿል።

ጤናማ የኑሮ ልማድን እና ንጹህ ትራንስፖርትን ለማበረታታት የታሰበዉ ይህ ፌስቲቫል በውስጡ የብስከሌት የጋራ ጉዞ (Group Ride) የመንገድ ደህንነት ስልጠና፣ ለህጻናት እና ለቤተሰብ የሚመች መዝናኛ ፕሮግራሞችን እንዲሁም የኮሪደር እና ቱሪዝም መዳረሻዎች ጉብኝትን ማስተዋወቂያዎች የያዘ መሆኑ ተነግሯል።

የብስክሌት ውድድሩ በየወሩ የሚካሄድ ሲሆን አንደኛው ዙር ውድድር የፊታችን እሁድ የካቲት 01/2018 ዓ.ም የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ወጣቶችና ፍላጎት ያላቸው በነጻ የሚሳተፉበት ፒያሳ አራዳ ፓርክ ይካሄዳል፡፡

ይህ ፕሮግራም በከተማችን ውስጥ የብስክሌት ባህልን ለማሳደግ፣ የአካል እንቅስቃሴን ለማበረታታት እና ንጹህ አካባቢ ለመጠበቅ የሚያግዝ ነው።

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.