Logo
FIDEL POST NEWS
የቅጥር/የምዝገባ ማስታወቂያ ለጤና ባለሙያዎች በሙሉ!

​የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር የጤና ተቋማትን የአገልግሎት ጥራትና ደህንነት ይበልጥ ለማሻሻል የጤና ቁጥጥር ስርዓቱን ዲጂታላይዝድ (Digitalized) እያደረገ ይገኛል።

​በመሆኑም ይህንን ዘርፈ ብዙ የቁጥጥር ስራ በብቃት ለማከናወን የቁጥጥር ዘርፉን ለማገዝ ፈቃደኛ የሆናችሁ ባለሙያዎች ከዛሬ ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እንድትመዘገቡ ተጋብዛችኋል።

​📋 ተፈላጊ የትምህርት ዝግጅቶች

​ስፔሻሊስት እና ጠቅላላ ሃኪሞች
​ጤና መኮንኖች
​የላቦራቶሪ፣ የፋርማሲ እና የአንስቴዢያ ባለሙያዎች
​ነርሶች እና ሚድዋይፈሪዎች
​ባዮሜዲካል ኢንጂነሮች እና ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂስቶች
​የአካባቢ ጤና አጠባበቅ እና ሌሎች ተያያዥ የጤና ባለሙያዎች

​📌 ዋና ዋና መስፈርቶች

​እውቅና ካለው ተቋም የተመረቀ/ች እና የታደሰ የሙያ ፈቃድ ያለው/ላት።
​ከሚሰሩበት ተቋም የሥራ ልምድ እና የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
​የመስመር ላይ (Online) ስልጠና ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆኑ።
​በቁጥጥር፣ በክሊኒካል ኦዲት ወይም በጥራት ማሻሻል (Quality Improvement) ላይ ልምድ ያላቸው ይበረታታሉ።

​📑 እንዴት መመዝገብ ይቻላል?
​ባለሙያዎች የትምህርት ማስረጃ (Degree)፣ የታደሰ የሙያ ፈቃድ፣ የሥራ ልምድ እና ተያያዥ የሥልጠና ሰርተፊኬቶችን በPDF በማያያዝ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመዝገብ ይችላሉ፡

​🔗 የምዝገባ ሊንክ፡ https://forms.gle/fV4vKAJL...
​ለበለጠ መረጃ፡
📧 ኢሜይል፡ semreselam.tsegamoh.gov.et / hiwot.abebemoh.gov.et
🌐 ድህረ-ገጽ፡ moh.gov.et

​የጤና ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ 
4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.