Logo
Getu Temesgen
🔴⚪️ መድፈኞቹ በኤላንድ ሮድ ነጎዱ!
አርሰናል 4 - 0 ሊድስ ዩናይትድ 🔥
#ethiopia | ​"ዙቢሜንዲ እና ዮኬሬሽ ጎል አስቆጥረዋል፤ መሪነቱ ይበልጥ ተጠናክሯል!"

​በ24ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ከሜዳው ውጭ ወደ ኤላንድ ሮድ ተጉዞ ሊድስ ዩናይትድን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት በመርታት የሊጉን መሪነት አጠናክሯል።

​የጨዋታው ድምቀቶች:
⚽️ ማርቲን ዙቢሜንዲ እና የሊድሱ ግብ ጠባቂ ካርል ዳርሎ (በራሱ ላይ) ባስቆጠሯቸው ግቦች አርሰናል የመጀመሪያውን አጋማሽ 2-0 በመምራት አጠናቀቀ።

⚽️ ከእረፍት መልስ አዲሱ ኮከብ ቪክተር ዮኬሬሽ እና ጋብሬል ጀሱስ ተጨማሪ ግቦችን በማስቆጠር ድሉን አሳምረውታል።

​በዚህ ድል አርሰናል ወደ ዋንጫው የሚያደርገውን ጉዞ በልበ ሙሉነት ቀጥሏል።

የዛሬውን የአርሰናል አቋም እንዴት አያችሁት?

​#arsenal #coyg #premierleague #leedsunited #zubimendi #gyokeres #jesus #victory #epl #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.