ቬሮኒካ በሀገሯ ሽልማት አለማግኘቷ ያሳፍራት እንደነበር ገልጻለች።
#fastmereja I ታዋቂዋ ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ በሙያ ዘርፏ ያለፈችባቸውን አምስት ዓመታትና ያጋጠሟትን ፈተናዎች አስመልክቶ በሰጠችው አስተያየት፣ በሀገር ውስጥ የሚሰጡ ሽልማቶች ላይ ያላትን ቅሬታ በግልጽ አጋርታለች። በተለይም ከውጭ ሀገር አርቲስቶች ጋር ለስራ ስትነጋገር "ምን ሽልማት ወስደሻል?" ተብላ ስትጠየቅ በሀገሯ ሽልማት አለማግኘቷ ያሳፍራት እንደነበር ገልጻለች።
ቬሮኒካ በጽሁፏ ሁለት ዋና ዋና አካላት ላይ ትዝብቷን ጥላለች፦
📌 የሽልማት አዘጋጆች፦ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታወቁ ስራዎችን ብትሰራም፣ ተገቢውን እውቅና እና ሽልማት አለመስጠታቸውን።
📌 የመንግስት አካላት፦ አርቲስቶች ሀገራቸውን በአለም አቀፍ መድረክ ሲያስተዋውቁ የሚሰጠው ድጋፍ እና ትኩረት ማነስ።
"መንግስት እንደ ትልቅ ጉዳይ አድርጎ ባያየንም፤ ባይደግፈንም፤ ሰርተን የመጣነው ሀገር ማስተዋወቅ ምናልባት ሌላ ሀገር ቢሆን ብዙ የሚመሰገንበት ጉዳይ ነበር" — ቬሮኒካ አዳነ
📌 አዲስ ድል በሩዋንዳ (Shining Star Africa Awards)
በሀገር ውስጥ ባይሆንም፣ በአህጉር አቀፍ ደረጃ ግን የቬሮኒካ ስራዎች ትልቅ እውቅና እያገኙ ይገኛሉ። ቀደም ሲል በህዝብ ድምፅ ሶስት ሽልማቶችን ማሸነፏን ያስታወሰችው ድምፃዊቷ፣ አሁን ደግሞ በሩዋንዳ በሚካሄደው Shining Star Africa Awards 2025/2026 ላይ በሁለት ትልልቅ ዘርፎች እጩ መሆኗን አብስራለች፦
📍Best Star Global Artist Of The Year
📍Best Star Female Artist Of The Year
ቬሮኒካ በዚህ የሽልማት መድረክ ላይ በመጀመሪያዋ እና ብቸኛዋ ኢትዮጵያዊት ሴት አርቲስት በመሆን መታጨቷ ለሙያዋ ያላትን ቁርጠኝነት እና የአለም አቀፍ ተቀባይነቷን የሚያረጋግጥ ሆኗል።

6 months ago