የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ፤ የኢራን ሰባት ዕጣ ፈንታዎች!
ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀታቸውን ተከትሎ፣ የቀጣናው የደህንነት ባለሙያ የሆኑት ፍራንክ ጋርድነር ሰባት ሊከሰቱ የሚችሉ ሁኔታዎችን እንደሚከተለው አስቀምጠዋል፡
1️⃣ የዲሞክራሲ ሽግግር፦ የአብዮታዊ ዘበኛ ወታደራዊ ሰዎች ላይ የሚሰነዘር ጥቃት የኢራንን አገዛዝ ሽባ በማድረግ ሀገሪቱ ወደ እውነተኛ ዲሞክራሲ እንድትሸጋገር መንገድ ሊከፍት ይችላል።
2️⃣ የአገዛዙ ፖሊሲ መቀየር፦ አገዛዙ ባይወድቅ እንኳ፣ በደረሰበት ጥቃት ተዳክሞ የኒውክሌር መርሃ ግብሩን እንዲያቆም እና የሚሊሻዎች ድጋፉን እንዲያቋርጥ ሊገደድ ይችላል።
3️⃣ የወታደራዊ መንግስት ምስረታ፦
በጥቃቱ ሳቢያ ሀገሪቱ ወደ ትርምስ ውስጥ ከገባች፣ የአብዮታዊ ዘበኛው ከፍተኛ መኮንኖች ስልጣኑን በመቆጣጠር ወታደራዊ አምባገነንነትን ሊመሰርቱ ይችላሉ።
4️⃣ የኢራን የአጸፋ ጥቃት፦ ኢራን ያላትን የባሊስቲክ ሚሳኤል እና የድሮን ክምችት በመጠቀም በባህሬን እና ኳታር የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችን ኢላማ ልታደርግ ትችላለች።
5️⃣ የሆርሙዝ ወንዝ መዘጋት፦ ኢራን የአለም 25% የነዳጅ ንግድ የሚያልፍበትን የሆርሙዝ ወንዝ ከዘጋች፣ የአለም የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ሊንርና ኢኮኖሚው ሊናጋ ይችላል።
6️⃣ የአሜሪካ የጦር መርከብ መስጠም፦ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፈጣን ጀልባዎችን እና ድሮኖችን በአንድ ጊዜ በማሰማራት የአሜሪካን ግዙፍ የጦር መርከብ ለማጥቃት ሙከራ ሊደረግ ይችላል።
7️⃣ የእርስ በርስ ጦርነትና የሰብአዊ ቀውስ፦ የ93 ሚሊዮን ህዝብ ባለቤት የሆነችው ኢራን ወደ ትርምስ ከገባች፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞችን የሚያፈራ አዲስ ቀጠናዊ ቀውስ ሊከሰት ይችላል።
ምንጭ፡ BBC Security Analysis

6 months ago