Logo
FIDEL POST NEWS
ትራምፕ ወደ ኢራን "ግዙፍ የጦር መርከቦች" (Armada) መላካቸውን አስታወቁ

​ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአክሲዮስ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ሁኔታ "እየተቀየረ" መሆኑን ገልጸዋል።

ለዚህም ምክንያት የሆነው አሜሪካ ወደ ቀጣናው የላከችውና ከቬንዙዌላ አቅራቢያ ከነበረው የሚበልጥ "ግዙፍ የአርማዳ ጦር" ነው ብለዋል።

​የጦር ዝግጅት፦ የUSS Abraham Lincoln የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ እና ሌሎች አጃቢ የጦር መርከቦች ሰኞ እለት ወደ መካከለኛው ምስራቅ መግባታቸው ተረጋግጧል።

በተጨማሪም F-35 እና F-15 ተዋጊ ጄቶች በተጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ።

​የጥቃት አማራጭ፦ የኢራን አገዛዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን መግደሉን ተከትሎ፣ ትራምፕ ወታደራዊ እርምጃን እንደ አንድ አማራጭ ይዘውታል። "ውሳኔው ገና አልተላለፈም፣ ነገር ግን ዝግጁ ነን" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

​ድርድር፦ ወታደራዊ ጫናው ቢኖርም፣ ትራምፕ "ኢራን ድርድር ትፈልጋለች፣ ደጋግመው ደውለውልናል" በማለት ዲፕሎማሲያዊ መንገድ አሁንም ክፍት መሆኑን ጠቁመዋል።

​የአሜሪካ ቅድመ ሁኔታዎች፦ ማንኛውም ስምምነት የኢራንን የዩራኒየም ክምችት ማስወገድ፣ የረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን መገደብ እና የሽብር ቡድኖችን መርዳት ማቆምን ማካተት እንዳለበት ዋይት ሃውስ አስታውቋል።

​🔍 ዳራ፦ ባለፈው ሰኔ ወር ላይ እስራኤልን ጨምሮ በሁለቱ ሀገራት መካከል ለ12 ቀናት የዘለቀ ግጭት መከሰቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ትራምፕ በወቅቱ የኢራን የኒውክሌር ተቋማት ላይ ጥቃት እንዲሰነዘር በማድረግ "ኢራን የኒውክሌር ባለቤት እንዳትሆን አድርጌያለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.