የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሁሉም ባንኮች ለተመረጡ የገቢ ዕቃዎች የብድር ሰነድ (LC) ወይም ሌሎች የክፍያ መንገዶችን ሲፈቅዱ፣ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሚያወጣውን ተመን እንደ አመላካች ዋጋ እንዲጠቀሙ ግዴታ ጣለ።
ብሔራዊ ባንኩ ዛሬ ጥር 17 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ይህ ውሳኔ ተግባራዊ የሚደረገው ከማክሰኞ ከጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ነው።
ባንኩ ውሳኔውን ያስተላለፈው በቅርቡ ባደረገው ክትትል፣ ባንኮች ለብድር ሰነድ የሚጠቀሙባቸው ዋጋዎች ከጉምሩክ ኮሚሽን የማጣቀሻ ዋጋዎች ጋር ሲነፃፀሩ ከፍተኛ ልዩነት እንዳላቸው ካረጋገጠ በኋላ መሆኑን ገልጿል።
ይህም በባንክ ሥርዓቱና በጉምሩክ ኮሚሽን መካከል ያለውን የዋጋ ልዩነት ለማስወገድና የውጭ ምንዛሪ መረጃዎችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እንደሚረዳ ታምኖበታል።
እንደሚታወሰው፣ ብሔራዊ ባንክ በሐምሌ 2016 ዓ.ም ተግባራዊ ባደረገው የውጭ ምንዛሪ መመሪያ፣ የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ እንዲወሰን ማድረጉ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ቀደም ሲል የነበረው ዝቅተኛ የገቢ ዕቃዎች ዋጋ መመሪያ (Minimum Price Directive) ተሰርዞ፣ የገቢ ዕቃዎችን ዋጋ ትክክለኛነት የማረጋገጥ ኃላፊነት ለባንኮች ተሰጥቶ ነበር።
አዲሱ መመሪያ ባንኮች የጉምሩክ ዋጋን እንደ ማጣቀሻ እንዲጠቀሙ በማድረግ፣ በገበያው ውስጥ የሚታየውን የዋጋ አለመጣጣም ለማስተካከል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።via.capital
seledadotio

6 months ago