“ሕፃናትን ከልብ ሕመም ሞት እንታደግ”
#ethiopia | “ሕፃናትን ከልብ ሕመም ሞት እንታደግ” በሚል መሪ ቃል በኸርት ቱ ኸርት ቺልድረን ኤድ ፋውንዴሽን የቦርድ አባላት እና በኢትዮ-አሜሪካ የንግድ ምክር ቤት የልዑካን ቡድን አባላት የእግር ጉዞ መርሐግብር ተከናወነ።
በኢትዮጵያ ውስጥ በልብ ህመም የሚሰቃዩ ህጻናትን ለመርዳት እስካሁን ድረስ በኸርት ቱ ኸርት ቺልድረን ኤድ ፋውንዴሽን እህት ድርጅት በኾነው በኢትዮ-ኢስታንቡል አጠቃላይ ሆስፒታል በኩል ሙሉ ወጪያቸው ተሸፍኖ ከ85 በላይ ለሚሆኑ ህጻናት የቀዶ ጥገና ህክምና ሲደረግ መቆየቱ፣
ይህንኑ አገልግሎት በዘላቂነት ለማስቀጠል በኢትዮ ኢስታንቡል አጠቃላይ ሆስፒታል ባለቤት በአቶ ብርሃን ተድላ መስራችነት ኸርት ቱ ኸርት ቺልድረን ኤድ የተሰኘ የበጎ አድራጐት ድርጅት መቋቋሙ የሚታወስ ነው።
ፋውንዴሽኑን ይበልጥ ውጤታማ በማድረግ ረገድ በአሜሪካ ከሚገኙ የተለያዩ ግዛቶች የህክምና ቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ በስፋት ለማከናወን የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ በኢትዮ-አሜሪካ የንግድ ምክር ቤት እና በኸርት ቱ ኸርት ቺልድረን ኤድ ፋውንዴሽን መካከል ለልብ ታማሚ ህጻናት ሕክምና የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ስምምነት ጥር 7 ቀን 2018 ዓ.ም በአበባ አበባ ከተማ መፈረሙ እና በዕለቱም ከልዑካን ቡድኑ አባላት መካከል ወ/ሮ አበባ በየነ እና አቶ ፍጹም ተስፋዬ እያንዳንዳቸው ብር 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን ብር) በድምሩ 2,000,000 (ሁለት ሚሊዮን ብር) በሚሆን ወጪ ሁለት የልብ ህሙማን ህፃናትን ለማሳከም ቃል መግባታቸው ይታወሳል።
ትላንንት ማምሻውን የተካኼደው መርሐግብር በኸርት ቱ ኸርት ቺልድረን ኤድ ፋውንዴሽን እና በኢትዮ-አሜሪካ የንግድ ምክር ቤት መካከል የተደረገውን ስምምነት ምክንያት በማድረግ “ሕፃናትን ከልብ ሕመም ሞት እንታደግ” በሚል መሪ ቃል የፋውንዴሹኑ የቦርድ አባላት ከምክር ቤቱ የልዑካን ቡድን አባላት ጋር በመሆን በውቢቷ አዲስ አበባ የእግር ጉዞ ለማድረግ የተዘጋጀ መኾኑን አቶ መኮንን ሰሙ የፋውንዴሽኑ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ተናግረዋል።
በዚህ መርሐግብር ላይ የፋውንዴሽኑን ቦርድ በመወከል ባስተላለፉት መልዕክት በፍፁም ሰብዓዊነትና በበጎ አድራጎት መንፈስ የተነሳንለትን ዓላማ በመደገፍ ቅን ልብ ባላቸው ወገኖች እየተደረገ ያለውን ድጋፍ ቦርዱ በከፍተኛ ክብርና አድናቆት የሚመለከተው አኩሪ ተግባር በመሆኑ እጅ ለእጅ ተያይዘን የሕፃናትን ሰቆቃ ድል ማድረግ እንችላለነን ብለዋል።
የእግር ጉዞ መረርመግብሩ ዓላማ አንድነታችን መገለጫ በመሆኑ ቦርዱ ከፍተኛ ደስታና ኩራት የተሰማው መሆኑን እየገለፅኩ በቅንነትና በሩህሩህነታችሁ ነፍሳትን ለማትረፍ ስለታደላችሁና ስለተመረጣችሁ እናንተንም እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ። ለተሳታፊዎች በሙሉ በልብ ሕመም በሚሰቃዩት ሕፃናት ስም ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን ሲሉ መልዕክታቸውን አጠቃለዋል።

5 months ago