Logo
YenetaTube
ትላንት ጥር 8 ቀን 2018 ዓ.ም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለግብጹ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አል-ሲሲ በላኩት ደብዳቤ አሜሪካ በህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ በድጋሚ በሽምግልና ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።

ትራምፕ በደብዳቤያቸው ላይ በዚህ ቀጠና ያለ ማንኛውም ሀገር የዓባይን ሀብት ብቻውን መቆጣጠርና ጎረቤቶቹን መጉዳት የለበትም የሚል አቋም አንጸባርቀዋል።

ኢትዮጵያ ከግድቡ የምታመነጨውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለግብፅ እና ለሱዳን በነጻ እንድትሰጥ ወይም እንድትሸጥ የሚል ምክረ-ሃሳብ አቅርበዋል።

በተለይ በድርቅ ወቅት ግብፅ የምታገኘው የውሃ መጠን አስቀድሞ ታውቆ ዋስትና እንዲሰጠው ድርድር እንዲጀመር ፍላጎታቸውን ገልጸዋል።

ግድቡ በይፋ ግንባታው ተጠናቆ ካለፈው መስከረም ወር 2018 ዓ.ም (September 2025) ጀምሮ በሙሉ አቅሙ ስራ መጀመሩ ይታወሳል።

በአሁኑ ወቅት ከ5,000 ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ላይ ደርሷል።
ኢትዮጵያ የግድቡን የውሃ ሙሌት ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቋን ገልጻለች ይህም ለግብፅ ከፍተኛ ስጋት ሆኖባታል።

ግብፅ አሁንም ህጋዊ አስገዳጅ ስምምነትBinding Agreement ሳይኖር ኢትዮጵያ የምትወስደው ማንኛውም እርምጃ ተቀባይነት የለውም በማለት ላይ ትገኛለች።

ትራምፕ የላኩትን ደብዳቤም እንደ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል እየተመለከተችው ነው።

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ትራምፕ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የነበረው ሽምግልና ለግብፅ ያደላ ነበር በሚል ውድቅ ማድረጓ ይታወሳል።

አሁንም አዲሱ የትራምፕ አስተዳደር የሚያሳየው የአንድ ወገን ዝንባሌ በኢትዮጵያ በኩል ጥንቃቄ የተሞላበት ምላሽ እንዲሰጥ እያደረገ ነው።

ትራምፕ በደብዳቤያቸው መጨረሻ ላይ "ይህ በግድቡ ምክንያት የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ወታደራዊ ግጭት እንዳያመራ ተስፋ አደርጋለሁ" በማለት ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት አስተላልፈዋል።

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.