Logo
Getu Temesgen
🎨 የኪነ-ጥበብ መንደር በታሪካዊቷ ጎንደር! 🏰
#ethiopia | ​"ጎንደርን የኪነ-ጥበብ መናገሻ የሚያደርግ የጥናት ስራ ተጀምሯል።"

​የ«ኪን-ኢትዮጵያ» የጥበብ እና የባህል መድረክ የመጀመሪያ ሀገር አቀፍ ጉዞውን በጎንደር ከተማ ባደረገበት ወቅት አንድ ትልቅ ብስራት ተሰምቷል።

​ምን ተባለ?
የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው እንደገለጹት፤ ከተማዋ ያላትን የኪነ-ጥበብ አቅም ለመጠቀም እና ለባለሙያዎች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር "ዘመናዊ የኪነ-ጥበብ መንደር" ለመገንባት የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ ነው።

​በመድረኩ የተላለፉ ቁልፍ መልዕክቶች፡-
✅ ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ: "ኪነ-ጥበብ የአንድነታችን ማገር ነው" ሲሉ የጎንደር ህዝብ ላደረገው ኢትዮጵያዊ አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል።

✅ አቶ መልካሙ ጸጋዬ: በክልሉ ነጠላ ትርክቶችን በማክሰም አሰባሳቢ ትርክትን ለመፍጠር ኪነ-ጥበብ ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን ገልጸዋል።

​ይህ የኪነ-ጥበብ መንደር እውን ሲሆን ለሀገራችን ጥበብ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታመናል።

​ጌትነት ተመስገን

​#gonder #artvillage #ethiopianart #culture #unity #addisababa #kinethiopia #gonder #ethiopianarts

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.