ያንጎ ኢትዮጵያ፣ በገና በዓል ለሰላም የሕጻናት መንደር የበጎአድራጎት ድርጅት ድጋፍ አደረገ!
…
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ – ጥር 2018ዓ.ም.: ከጂቱጂ አይቲ ሶሉሽንስ እና ከኤሌጋንስ ኢምፖርት ኤንድ ኤክስፖርት ፒ.ኤል.ሲ በተጨማሪ ከተለያዩ የፍራንቻይዝ አጋሮች ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ሥራውን የሚያከናዉነዉ ያንጎ ኢትዩፒያ ፣ የገና በዓልን አስመልክቶ ለህጻናት እና ወጣቶች እንክብካቤ፣ ትምህርት እና ሁለንተናዊ እድገት ለሚተጋው ሰላም የህጻናት መንደር በጎ አድራጎት ድርጅት - አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን እና መጫወቻዎችን ለግሷል።
ያንጎ፣ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት በሰላም የህጻናት መንደር ለሚኖሩ 481 ህጻናት አስፈላጊ የሆኑ ምግቦችን፣ የንፅህና መጠበቂያ መገልገያዎችን እና መጫወቻዎችን አቅርቧል። ድጋፉ፣ 500 ኪሎ ግራም ስኳር፣ 48 ካርቶን ፓስታ፣ 481 ኪሎግራም ሩዝ፣ 962 የልብስ ማጠቢያ እና 966 የላይፍቦይ ንፅህና መጠበቂያ ሳሙናዎችና ዕቃዎች፣ እንዲሁም የልጆች መጫወቻዎችን ያካተተ ሲሆን ይህም አስፈላጊውን ግብዓት በማሟላት እፎይታን የሚሰጥ እና በበዓል ሰሞን መሆኑ ደግሞ ደስታን እንደሚፈጥር ታምኖበታል፡፡
በኢትዮጵያ የያንጎ ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ይቀናለም አበበ፣ በኢንሼቲቩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን ኩባንያው የኢትዮጵያ ገና፣ በመተሳሰብና በልግስና የሚከበር እንዲሁም ደማቅ ማኅበረሰባዊ እሴቶች ከፍ ብለው የሚታዩበት በዓል መሆኑን እንደሚያምን ተናግረዋል፡፡ አክለውም "የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ በሰላም የህፃናት መንደር በጎ አድራጎት ድርጅት የተደረገው የያንጎ ድጋፍ፣ ለምናገለግለው ማኅበረሰብ ያለንን ክብር ያሳያል። ሕጻናትን በመደገፍ እና ነገ ላይ የተሻለ ሕይወት እንዲገነቡ ለመርዳት በየቀኑ በትጋት ከሚሠሩ ድርጅቶች ጋር በአጋርነት መቆም፣ ትርጉም ያለውና ዘላቂ ተጽእኖ እንደሚያመጣም እናምናለን።" ብለዋል፡፡
ተነሣሽነቱ በአፍሪካ ውስጥ ሰፊ የያንጎ የማኅበረሰባዊ ኃላፊነት ጥረቶች አካልን የሚመሠርት ሲሆን ይህም በአካባቢው ላይ ባለ ጠንካራ አጋርነት ላይ የሚያጠነጥን፣ እውነተኛ የማኅበረሰብ ፍላጎቶችን በመረዳት ችግሮችንየሚፈታ እና ዘላቂነት ባላቸውን በጎ ማኅበራዊ አበርክቶዎች ላይ የሚያተኩር ነው።
በ1986 (ዓ.ም - እ.አ.አ.) የተመሠረተው ሰላም የሕጻናት መንደር የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችንና ወላጆቻቸውን ላጡና ለማጣት በአደጋ ላይ ያሉ ሕጻናትን በዘላቂ እና ትምህርትን፣ ጤናን፣ ማኅበረሰባዊ ሁነቶችን፣ አእምሯዊ ጤናን እና የኑሮ ክሂሎቶችን ባማከሉ ድጋፎች ማገዝ ከጀመረ አራት አሥርት ዓመታትን አሥቆጥሯል፡፡ ከ16 ዓመታት በፊት ግን፣ ተቋሙ አሠራሩ ላይ ለውጥ በማድረግ ልጆች በቤተሰብ መሐል አስፈላጊውን ቤተሰባዊ ድጋፍ፣ ፍቅር እና ጥበቃ አግኝተው እንዲያድጉ በማሰብ ወደ ቤተሰባዊ ሞዴል መንደርነት ተሸጋግሯል፡፡
በዚህ የገና በዓል ድጋፍ እና ተነሣሽነት ላይ ያንጎ፣ እንዲህ ዓይነት ማኅበረሰባዊ ግዴታቸውን በመወጣት ረገድ ቁርጠኛ አቋም ያላቸውን እና በጎ ማኀበረሰባዊ ለውጥ ለማምጣት የሚተጉ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችን ለመደገፍ እና ማኅበረሰባዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ከሚሰጠው የትራንስፖርትና የቴክኖሎጂ አገልግሎት ጎን ለጎን ሁልጊዜም ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል፡፡
- ###-
#ስለያንጎ ግሩፕ
ያንጎ ግሩፕ፣ ዋና መሥሪያ ቤቱን በዱባይ ያደረገ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ዘመን አፈራሽ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ዕለታዊና ኑሮን የሚያቀሉ አገልግሎቶች በመቀየር ማኅበረሰቦችን የሚያገለግል ተቋም ነው። ለፈጠራ ባለው የማያወላውል ቁርጠኝነት፣ ከዓለም ዙሪያ መሪ ቴክኖሎጂዎችን ወደተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያለምንም እንከን ወደ የተቀናጀ የዕለት ተዕለት አገልግሎቶች ይቀይራል፤ በየጊዜውም ያዘምናል፡፡ ተልእኳችን መሪ የዓለም ፈጠራዎችን ለሁሉም በማዳረስ በዓለም ሕዝቦች መካከል ያለውን ልዩነት ማቃለል፣ ግንኙነቶችን ማጎልበት እና የዕለት ተዕለት የኑሮ ልምዶችን ማጎልበት ነው።
የያንጎ ባለብዙ-ተግባር መተግበሪያ በአፍሪካ፣ በላቲን አሜሪካ፣ በአውሮፓ እና በመካከለኛው ምሥራቅ ባሉ ከ20 በላይ ሀገራትውስጥ በርካታ የዲጂታል ከተማ አገልግሎቶችን ይሰጣል። የያንጎ ብዙ ቋንቋ ተናጋሪ መተግበሪያ በአንድሮይድ እና አይኦኤስ ላይ በነጻ ይገኛል።
#ስለ ሰላም የሕጻናት መንደር
በ1986 የተቋቋመው ሰላም የሕጻናት መንደር ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ መንግሥታዊ ያልሆነ እና ለትርፍ ያልተቋቋመ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችንና ወላጆቻቸውን ላጡና ለማጣት በአደጋ ላይ ያሉ ሕጻናትን በመደገፍ በሁለንተናዊ ድጋፍ ማለትም አእምሯዊ እና አካላዊ ደኅንነታቸው ተጠብቆ እንዲያድጉ፣ እንዲማሩ ብሎም የተሻለ ነገ እንዲኖራቸው ከሁሉም እኩል የተመቻቸ ዕድል እንዲያገኙ የሚሠራ ተቋምነው፡፡

7 months ago