Logo
Getu Temesgen
🏰 ጎንደር ለጥምቀት አሸብርቃ እንግዶቿን እየተቀበለች ነው!

* "እንኳን ተወለድክ መይሳው!"
#ethiopia | ​ዛሬ ጥር 6 ቀን 2018 ዓ.ም፤ ጎንደር በሁለት ምክንያት ድርብ ደስታ ላይ ናት። አንደኛው የጥምቀት እንግዶቿን እየተቀበለች ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የታሪክ ማህደርን የቀየሩት እና ለኢትዮጵያ አንድነት ዋጋ የከፈሉት የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ 207ኛ ዓመት የልደት ቀን ዛሬ መሆኑ ነው።

​በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET 162 ተሳፍረን አፄ ቴዎድሮስ ኤርፖርት ስንደርስ፤ ጎንደር የጀግንነት እና የመንፈሳዊነት ድባብ ተላብሳ ጠበቀችን።

​የጎንደር ቆይታችን ቅምሻዎች፡-
✈️ አቀባበል፡ በኃይሌ ሪዞርት እና ሆቴል የተደረገልን ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ የጉዞ ድካማችንን አስረሳን።

✨ ድባብ፡ ከተማዋ ገና ከወዲሁ የጥምቀትን ድምቀት ለብሳለች። ፋሲል ግንብም በግርማ ሞገስ እንግዶቹን እየተመለከተ ነው።

​በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እንዲሁም በባህል ጥበባት ሚዲያ ፎረም የተዘጋጀው ይህ ጉዞ፤ የታሪክ እና የባህል ድግስን ይዞ ይቀጥላል...

​መልካም የጥምቀት በዓል ለሁላችን!

​✍️ ጌትነት ተመስገን

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

​#gondar #timket #epiphany #emperortewodros #history #ethiopia #travel #culture

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.