የጋብቻ አፈፃፀም ስርዓቶች እና ዉጤቶቹ፡-
ከንብረት ማስተዳደር አንፃር
አለምሰገድ አብርሃም-፡- በማናቸዉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃ ና የህግ አማካሪ
ስልክ 0910 2113 65/0931775959
#ethiopia | መነሻ፡- ቤተሰብ የህብረተሰብ መሰረት ነዉ፡፡ለአመሰራረቱም መነሻ በመሆን የሚያገለግሉ ግንኙነቶችን በተመለከተ በመወለድ፤በጋብቻ እና በጉዲፈቻ ናቸዉ፡፡ ህብረተሰብም የአንድ ሀገር ህልዉና ነዉ፡፡ ቤተሰብ በህብረተሰብ ዉስጥ ታላቅ ማህበረሰባዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሚናን የሚጫወት ተቋም መሆኑንም ሚካድ አይደለም፡፡ጋብቻን በተመለከተ በሀገራችንም ሆነ ከሀገራችን ዉጪ ባሉ የህግ ምሁራን መካከል ወጥ የሆነ አተረጓጎም አንድነት ባይኖርም ጋብቻ ክቡር እና የተቀደስ ተቋም መሆኑን ግን ማንም የሚያጣዉ እዉነታ አለመሆኑ በመረዳት ይመስላል፤ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች፤በሀገራችንም በፌደራሉ መንግስት እና በክልሎቻንን ህገ-መግስቶች እና ከህገ-መንግስቶቹ በሚመነጩ የቤተሰብ ህጎች ጋብቻ ተገቢዉ እዉቅና እና ጥበቃ የተቸረዉ ተቋም የሆነዉ፡፡ በዉጤቱም ከላይ በተገለፁት ህጎች ፤በዋናነት የማግባት መብት እና በጋብቻ ግዜ የፆታ እኩልነት መብቶች ተገቢዉ ትኩረት የተሰጣቸዉ ስለመሆኑ በተግባርም ተጋቢዎቹ ንብረት ማፍራትን እና ማስተዳደርን ታሳቢ በማድረግ ህጎቹ የተቀረጹት ስለመሆኑ በዚች አጭር ፅሁፍ እንመልከት፡፡ እንዝለቅ!.
1/ የጋብቻ አፈፃፀም ስርዓቶች/አይነቶች
የተሻለዉ የፌደራሉ የቤተሰብ ህግ ለሶስት ዓይነት የጋብቻ ማስፈፀሚያ ስርዓቶች እውቅና ይሰጣል፡፡ አንድ በአንድ እንመለከት፡-
1.1/ በክብር መዝገብ ሹም ፊት የሚፈፀም ጋብቻ (ብሔራዊ ጋብቻ)
በክብር መዝገብ ሹም ፊት (የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በመባል የሚታወቅ ሲሆን፤ተግባር እና ሃላፊነቱም በመመርያ ቁጥር 145/2015 መሰረት፤ልደት፤ሞት፤እና ጋብቻ መዝጋቢ ተቋም ነዉ) ጋብቻዉ ተፈፅሟል የሚባለዉ በተሻሻለዉ የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 2 መሰረት ተጋቢዎቹ ጋብቻ እንደሚፈፅሙ በመረዳት እና በመስማማት በክብር መዝገብ ሹም ፊት ቀርበዉ ነፃ ፍቃዳቸዉን የሚሰጡበት ሆኖ የክብር መዝገብ ሹሙም ይህንኑ ነፃ ፍቃዳቸዉን የሚቀበልበት ስርዓት ነዉ፡፡
1.2/ በሀይማኖት ስርዓት መሰረት የሚፈፀም ጋብቻ
ይህ የጋብቻ አፈፃፀም ስርዓት በተሻሻለዉ የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 3 መሰረት ጋብቻዉ ተፈፅሟል ለማለት የሚቻለዉ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት በሀይማኖታቸዉ ወይም ከሁለቱ በአንዳቸዉ ሀይማኖት መሰረት የሚፀና ጋብቻ ለመፈፀም የሚያስፈልጉ ስርዓቶችን የፈፀሙ አንደሆነ ጋብቻዉ በሀይማኖት ስርዓት መሰረት ተፈፅሟል ማለት ይቻላል ፡፡ የሚያስፈልገዉን ስርዓት መፈፀም ማለት በተለያዩ ሃይማኖቶች ዉስጥ ያለዉን የጋብቻ ስርዓት በህግ ጥበቃ ለመስጠት ያለመ ነዉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በሀይማኖት ስርዓት መሰረት የተፈፀመ ጋብቻ መሆኑን ለመረዳት የሀይማኖቱን ስርዓት ማወቅ የግድ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡
1.3. በባህል ስርዓት መሰረት የሚፈፀም ጋብቻ
ሌላዉ በባህል ስርዓት መሰረት ጋብቻ ተፈፀመ ለማለት፤ ጋብቻዉ ተጋቢዎቹ በሚኖሩበት አካባቢ ባህል፤በተጋቢዎቹ ባህል ወይም ከተጋቢዎቹ ባህል በአንዱ መሰረት የሚፀና ጋብቻ ለመቋቋም የሚያስፈልገዉን ስርዓት የፈፀሙ እንደሆነ ጋብቻ ተፈፅሟል ማለት የሚቻል ስለመሆኑ የቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 4 ያስገነዝበናል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሶስቱ የጋብቻ መፈፀሚያ ስርዓቶች ዉጪ፤ከኢትዮጵያ ዉጪ የሚፈፅምን ጋብቻ እዉቅና በመስጠት ረገድ፤ የቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 5 ጥበቃ የሚሰጥ ሲሆን በዚህም ተጋቢዎቹ ኑሯቸዉን በመሰረቱበት ሀገር የጋብቻ አፈፃፀም ስርዓት መሰረት እስከፈፀሙ ግዜ ድረስ በሀገራችን ህግ እዉቅና መስጠቱ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ይህ ጋብቻ ጥበቃ ሊደረግለት የሚችለዉ ጋብቻዉ ለህግ እና ለሞራል ተቃራኒ ባልሆነ ግዜ ብቻ ነዉ፡፡ ለአብነትም፡- የተመሳሳይ ፆታ ግንኙት ከህግ ና ከሞራል አንፃር ጥብቅ ክልከላ ያለበት እና ያልተፈቀደ ተግባር በመሆኑ አዉቅና ሊሰጠዉ የሚገባ አለመሆኑን እንገነዘባለን፡፡
በሀገራችን ህግ ጋብቻ የሚፈጽምባቸዉ ስርዓቶች የተለያዩ ቢሆንም ተመሳሳይ የህግ ዉጤቶች ያሏቸዉ ሲሆን 1ኛዉ ጋብቻ በንብረት ረገድ የሚኖረዉ ዉጤት ሲሆን ፤2ኛ በተጋቢዎቹ ግላዉ ግንኙት ላይ የሚኖረዉ ዉጤት ናቸዉ፡፡ ከእነዚህ ሁለት ዉጤቶች መካከል በዚህ አጭር ፅሁፍ አማካኝነት የምንመለከተዉ በንብረት ረገድ የሚኖረዉን ዉጤት ይሆናል፡፡
2/ ጋብቻ በንብረት ረገድ ያለዉ ዉጤት
በየትኛዉም የጋብቻ ስርዓት መሰረት ጋብቻዉ ቢፈፀምም፤ጋብቻ ህጋዊ ተግባር እንደመሆኑ መጠን በተጋቢዎች ላይ የሚፈጥረዉ ዉጤት ይኖራል፤ የተሻሻለዉ የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 40 ልብ ይሉኃል፡፡ በዚህም የጋራ ንብረት እና የጋራ እዳ እንደሚኖረዉ ሁሉ የግል ንብረት እና የጋራ እዳ እንደሚኖር ቀጥለን እንመልከት፡፡
2.1/ የባል እና ሚስት የግል ንብረት፤
ተጋብተዉ የሚኖሩ ባል ና ሚስት በጋብቻ ዉስጥ እያሉም ቢሆን የግሌ ንብረት ሊሉት የሚችሉት ንብረት ሊኖራቸዉ እንደሚችል በቤተሰብ ህጋችን ተመላክቷል፡፡ ይህም ማለት ባል ና ሚስቱ ጋብቻ ስለፈፀሙ ብቻ የግል ንብረቶቻቸዉ የጋራ ይሆናል ወይም ንብረቱ ከጋራ ንብረታቸዉ ጋር ይቀላቀላል ማለት እንዳልሆነ ያስገነዝበናል፡፡
በተሻሻለዉ የቤተሰብ ህጋችን አንቀፅ 57 መሰረት ያለ ግብይት የተገኙ ንብረቶችን በተመለከተ ጋብቻዉን በሚፈጽሙበት ግዜ በየግል የነበሯቸዉ ንብረቶች ወይም ከጋብቻ ቡኃላ በዉርስ ወይም በስጦታ በየግላቸዉ ያገኙዋቸዉ ንብረቶች የግል ንብረቶቻቸዉ ሆነዉ ይቆጠራሉ፡፡
ከዚህ የምንረዳዉ ሁለቱ ተጋቢዎች እስከ ጋብቻቸዉ ቀን ድረስ በየግላቸዉ የነበሯቸዉ ማናቸዉም ተንቀሳቃሽም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረቶች የግል ንብረቶቻዉ መሆናቸዉ እንደተጠበቀ ሆኖ ከጋብቻቸዉ ቡኃላም ቢሆን ከተጋቢዎቹ እንዱ በዉርስ ወይም በስጦታ በግል ያገኛቸዉ ንብረቶች በፈቃዳቸዉ የጋራ እንዲሆን ካልተስማሙ በቀር የግል ንብረቶቻቸዉ ሆነዉ ይቀጥላሉ፡፡
እነዚህ ንብረቶች ያለ ግብይት የተገኙ ንብረቶች የሚባሉ ሲሆን የመገኛ ምንጫቸዉን መሰረት በማድረግ ስያሜያቸዉን ያገኙ ሲሆን በዚህም፤ በዋጋም ይሁን ያለ ዋጋ (እንካ በእንካ) ያገኟቸዉ ባለመሆናቸዉ ነዉ፡፡ ይህ የህጉ መርህ ሲሆን ተጋቢዎቹ በስምምነት ቀሪ ሊያደርጉት መሻታቸዉ የሆነ እንደሆነ ስጦታዉ ወይም ኑዛዜ ለሁለቱም እንዲሆን በማድረግ ንብረቱ የጋራ ንብረታቸዉ እንዲሆን ማድረግ ይቻላቿል፡፡
ሁለተኛዉ የግል ንብረት አይነት በግብይት የተገኘ ሆኖ ሚስት ወይም ባል ከጋብቻ በፊት የነበራቸዉን ንብረት በጋብቻ ግዜ በመሸጥ ሌላ ቢገዙ ወይም በቀጥታ በሌላ ንብረት ቢቀይሩት በግብይት የተገኘ ንብረት ስለሚሆን የጋራ ንብረት ይሆናል፡፡ ይህ በግብይት የተገኘዉ ንብረት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የጋራ ንብረት ይሆናል፡፡
በሌላ በኩል ህጉ ይህንን ሁኔታ በመገንዘብ ይመስላል መዉጫን አዘጋጅቷል፡፡ መዉጫዉም በተሻሻለዉ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 58(3) መሰረት ንብረቱ ከጋራ ንብረትነት እንዲገለልለት አቤቱታ በማቅረብ የግል ንብረቴ ነዉ ማስባል ማስባል እንደሆነ እንረዳለን፡፡ የዚህ ልዩ ሁኔታ ዓላማ የግል ንብረት ከጋራ ንብረት ጋር እንዳይቀላቀል ማስቻልን ታሳቢ ያደረግ ነዉ፡፡
በምሳሌ ይህንን ጉዳይ እንመልከት፡- የግሉ መኪና የነበረዉ ተጋቢ መኪናዉን ሸጦ ቤት የገዛ እንደሆነ በተሻሻለዉ የቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 57 መሰረት አዲስ የተገዛዉ ቤት አቤቱታ በሌላኛዉ ተጋቢ ለፍርድ ቤት ቀርቦ እስኪገለል ድረስ የባል ና ሚስቱ የጋራ ንብረት ይሆናል ( አንቀፅ 62(1)፡፡ ይህ እንዳይሆን፤ ንብረቱ የጋራ አይደለም፤ የግሌ ንብረት ነዉ የሚል ቢሆን ሌላኛዉ ተጋቢ በቤተሰብ ሕጉ አንቀፅ 58(3) መሰረት ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርቦ ከጋራ ንብረትነት አዲሱን በግዥ የተገኘዉን ንብረት ማግለል እንዲችል መብጡ ተጠብቋል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ሊታይ የሚገባዉ ነጥብ የግል ንብረቴ ነዉ የሚለዉ ተጋቢ በግብይት የጋራ የሆነዉን ንብረት ለፍርድ ቤት አቤቱታ በማቅረብ ለማስገለል የግዜ ገደብ ያለበት ስለመሆኑም ( በተሻሻለዉ የቤተሰብ ህግ ላይ ይህንን በተመለከተ ያለዉ ነገር ባይኖርም መደበኛዉን የፍታብሄር ህጉን ደንቦች መመለክት ተገቢነት አለዉ) ልብ ሊባል የሚገባዉ ጉዳይ ነዉ፡፡
ሌላዉ የግል ንብረት አስተዳደርን በተመለከተ ፤ ከተጋቢዎቹ የግል ንብረቴ ነዉ የሚለዉ ተጋቢ ገደብ የሌለበት መሆኑን ነዉ፡፡ ይሄ ሲባል ከንብረቱ የሚገኘዉን ፍሬ መጠቀምን በተመለከተ በሌላኛዉ ተጋቢ የጋራ ባለመብትነት የተገደበ መሆኑ ልብ ሊባል የሚገባ ነዉ (የተሻሻለዉ የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 62(1)፡፡
ይህንን ጉዳይ በምሳሌ ተመልክተን ወደ 2ኛዉ ነጥብ እንለፍ፡፡ አንደኛዉ ተጋቢ በግብይት ያልተገኘ የግሉ ንብረት የሆነዉን ቤት በማከራየት ገቢ ማግኘቱን ተከትሎ ከኪራዩ የሚገኘዉ ገቢ የጋራ ገቢ ይሆናል፡፡
ለዚህም የተሻሻለዉን የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 59(2) መመልከቱ በቂ ነዉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ንብረቱ የግል መሆኑ የተረጋገጠለት አንደኛዉ ተጋቢ ይህንን ንብረቱን የማስተዳደር መብቱን በተመለከተ በጋብቻ ዉል አልያም ደግሞ በዉክልና ለሌላኛዉ ተጋቢ ማስተላለፍ የሚቻለዉ ስለመሆኑ በተሻሻለዉ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 60 እና 61 ላይም በግልጽ ተቀምጦ እናገኛለን፡፡
2.2 የባል ና ሚስት የጋራ ንብረቶች፤
የባል እና ሚስት የጋራ ንብረቶች በተመለከተ ፤ ተጋቢዎቹ ከጋብቻቸዉ አስቀድመዉ የግል ንብረቶች ኖሯቸዉ ነገር ግን ጋብቻቸዉን በፈፀሙ ግዜ በጋብቻ ዉላቸዉ አማካኝነት የጋራ ንብረቶች እንዲሆኑ መስማማትን ህጉ በግልጽ ፈቅዷል፡፡ ይህ ንብረቱን የጋራ የሚያደርገዉ የጋብቻ ዉል በህግ ፊት ተቀባይነት ይኖረዉ ዘንድ በፅሁፍ መደረግ፤በአራት ምስክሮች (4) መፈረም እና ይህ የጋብቻ ዉል አንዱ ቅጂ በፍርድ ቤት ወይም በክብር መዝገብ ሹም ፊት መቀመጥ ያለበት ስለመሆኑ በአስገዳጅነት አስቀምጧል፡፡ የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች ባልተሟሉ ግዜ ግን ዉሉ ተቀባይነት ሊኖረዉ የሚችል አይደለም፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጋራ ንብረቶች ስንል ምን ምን ንብረቶችን የሚመለከት እንደሆነ ከተሻሻለዉ የቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 62 ላይ እንመልከት፡-
ከግል ጥረታዉ የሚያገኟቸዉ ገቢዎቸ፤
ከግል ወይም ከጋራ ንብረት የሚገኝን ገቢ፤
በቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 58(2) መሰረት የአንደኛዉ ተጋቢ ሀብት ነዉ ያልተባለ በግይት የተገኘ ንብረት፤( ያልተገለለ ንብረት)
ተጋቢዎች በጋራ በተደረገላቸዉ ስጦታ ያገኙት ንብረት (የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 62(3) እንዲሁም ፤
ተጋቢዎች በኑዛዜ ያገኙት ንብረት የጋራ ንብረት ሲሆን ይህም በቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 57 ላይ ተመላክቶ እናገኛለን በሌላ በኩል
በቤተሰብ ህጉ የግል ይሁን የጋራ ንብረቶች ስለመሆናቸዉ የሚያጠራጥሩ ንብረቶችን ወይም የሀብት ምንጮችን በተመለከተ የቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 63 መሰረት አንደኛዉ ተጋቢ የግል ሀብቱ መሆኑን የማስረዳ ሸክምን በመስጠት፤አንደኛዉ ተጋቢ የግል ንብረቱ መሆኑን ካላስረዳ በስተቀር ማንኛዉም ንብረት በሌላ ተጋቢ ስም ስመ-ሀብቱ ያለ እንኳን ቢሆን የጋራ ሀብት እንደሆነ የሕግ ግምት ይወሰዳል፡፡
ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ይሆነን ዘንድ ከተጋቢዎቹ አንዳቸዉ የሎተሪ እጣ የደረሳቸዉ እንደሆነ ሎተሪዉ የደረሰዉ ተጋቢ በተመለከተ የግል እንዳይባል ከቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 57 እና 58 ዉጪ ነዉ፤ የጋራም ተብሎ እንዳይባል ከአንቀፅ 62 ዝርዝር ዉጪ በመሆኑ በህግ ግምት አንቀፅ 63 መሰረት የጋራ ሀብት ሆኖ ይጠቃላል፡፡ ከእነዚህ ድንጋጌዎች መረዳት የሚቻለዉ በቤተሰብ ህጉ የግል ሀብት ልዩ ሁኔታ ሲሆን የጋራ ሀብት መርህ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡
2.3/ የተጋቢዎች የጋራ ሀብት አስተዳደር፤
የግል ሀብት አስተዳደርን በተመለከተ ራሱ አንደኛዉ ተጋቢ እንደሚጠነቀቅለት እና እንደ አስፈላጊነቱ በጋብቻ ዉል አልያም ደግሞ በዉክልና ሌላኛዉን ተጋቢ መሾም እንደሚችል ከላይ የተመለከትነዉ እንደተጠበቀ ሆኖ የእኩልነት መርህን በህገ-መንግስቱ እና በተሻሻለዉ የቤተሰብ ህግ ላይ ባለዉ መሰረት ፤የእኩልነት መርህ ገቢራዊ ከሚደረግባቸዉ አንዱ መንገድ የጋራ ሀብትን በእኩልነት መንፈስ ማስተዳደር መቻል ነዉ፡፡
ከዚህ አንፃር መደበኛ ገቢ አስተዳደርን እንመልከት ባል ና ሚስቱ ከየግል ጥረታቸዉ የሚገኙትን ገቢ የሚመለከት ሲሆን፤ ምንጩ የግል ጥረት ቢሆንም እንኳን ገቢዉ ግን የጋራ ሀብት ነዉ (አንቀፅ 62(1))፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ባል እና ሚስቱ በየግላቸዉ የሚያገኙት ገቢ በተመለከተ በየግላቸዉ የመቀበል መብታቻዉ እንደተጠበቀ ሆኖ በየስማቸዉ አልያም በጋራ በተከፈተዉ የቁጠባ ሂሳብ ማስቀመጥ እና ለጋራ ጥቅማቸዉ ማንቀሳቀስም የተፈቀደ ነዉ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ መነሣት ያለበት ነጥብ የግልጽነት ጉዳይ ሲሆን ይህም የገቢ መጠንን የሚመለከት ነዉ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከስምምነት አልያም ከፍርድ ቤት በሚነጭ ልዩ ሁኔታ አንደኛዉ ተጋቢ የሌላኛዉን ገቢ የመቀበል መብት ሊኖረዉ ይችላል ( የተሻሻለዉ የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 65)፡፡
ከፍርድ በሚነጭ ልዩ ሁኔታ ገቢን ሌላኛዉ ተጋቢ የሚቀበልበት ሁኔታ (ገደብ የተደረገበት ምክንያት) መሰረቱ የቤተሰቡን ጥቅም የሚጎዳ ( አባካኝነት) ሆኖ በሌላኛዉ ተጋቢ የሚፈፅም ተግባር እንደሆነ እና የመብት ገደብ እንዲደረግ አቤቱታ የሚያቀርበዉ ሌላኛዉ ተጋቢ ይህንን ለፍርድ ቤቱ ያስረዳ እንደሆነ ገቢን የመቀበል መብት(ነፃነት) ላይ ፍርድ ቤቶች እንደ ነገሩ ሁኔታ (mutatis mutandis ) ገደብ ሊጥሉ ይችላሉ፡፡
በሌላ በኩል የጋራ ንብረቱን የማስተዳደር መብት በስምምነትም ይሁን በፍርድ ቤት ዉሳኔ ያገኘ ሰዉ የንብረቱን አስተዳደር በተመለከተ ለሌላኛዉ ተጋቢ መረጃ የመስጠት ግዴታን ያለበት ስለመሆኑ ( የተሻሻለዉ የቤተሰብ አንቀፅ 67) መመልከቱ እዚህ ላይ ተገቢነት ያለዉ ነዉ፡፡
በሌላ በኩል እዚህ ላይ በትልቁ ልናየዉ የሚገባን ጉዳይ ቢኖር በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 34(1) እና በተሻሻለዉ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 66 መሰረት የእኩልነት መርህ ከጋራ ንብረት አስተዳደር አንፃር ገቢራዊ ከሚሆኑባቸዉ ተግባራት መካከል እና የተጋቢዎች ይሁንታ ከሚያስፈልግባቸዉ ቅድመ ሁኔታዎች መካከል የማይንቀሳቀስ ንብረትን (ቤት እና መሬት) ለመሸጥ፤ለመለወጥ ፤ለማከራየት ፤በመያዣ ወይም በዋስትና ለመስጠጥ ወይም በሌላ በማናቸዉም ሁኔታ ለሌላ ሶስተኛ ወገኖች መብት ለመፍጠር ከማሰብ አስቀድሞ፤ የሁለቱ ተጋቢዎች ስምምነት የሚያስፈልግ መሆኑን ልብ ሊባል ይገባል (የተሻሻለዉ የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 68)፡፡
ይህንን ግዴታ ተጋቢዎች ባልፈፀሙ ግዜ በሌላኛዉ ወገን አላግባብ የተደረገዉ ዉል እንዲፈርስ ለፍርድ ቤት ጥያቄ ማቅረብ የሚቻል ስለመሆኑ በቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 69 ላይ ተመላክቷል፡፡ በሌላ በኩል ከቅን ልቦና በመነጨ ሁኔታ ወደ ግብይቱ የገባዉን 3ኛ ወገን መብት እና ጥቅም ማሳጣት እና ገደብ ማበጀቱ የንብረት ግብይት ስርዓት ላይ የራሱ ሆነ አሉታዊ ተፅኖ ያለዉ በመሆኑ እና በግብይት ስርዓቱ ላይ እምነት የሚያሳጣም እንዳይሆን ህግ የግዜ ገደብ ያበጀ ሲሆን ይህም ተጋቢዎቹ ከቅን ልቦና ዉጪ በዘፈቀደ ዉል እንዲፈርስላቸዉ መጠየቅን መቋጫ ለማበጀት በማሰብ ደንብ አበጅቷል፡፡ ከዚህ የምንረዳዉ የተጋቢዎችን ኢኮኖሚያዊ መብት እና ጥቅም በማስጠበቅ ዉስጥ የግብይት ስርዓቱን (security of transaction) ሚዛን ቸል አለማለቱን እንገነዘባለን፡፡
2.4 የባል እና የሚስት እዳን በተመለከተ ( አንቀጽ 70-71)
ባል እና ሚስቶች የጋራ ንብት እንዲኖራቸዉ ህጉ የሚፈቅደዉን ያህል የጋራ እዳ ሊኖራቸዉ የሚችል ስለመሆኑ እና ይህንንም በተመለከተ የእዳዎቹን አይነት በዝርዝር ያስቀምጣል፡፡ ዕዳዉም በአንድነት ወይም በተናጠል ሆኖ መሰረቱም ከህግ፤ከዉል ወይም ከዉል ዉጪ ባለ ሁኔታ ሊሆን ይችላል፡፡
በተሻሻለዉ የቤተሰብ ህጋችን ፤የጋራ እዳ ቅድሚያ የሚጠየቀዉ ከጋራ ሀብት እንዲሆን ሲሆን በሌላ መልኩ ከተጋቢዎች የግል ንብረት ላይ የሚኬድበትን ሁኔታ በተመለከተ ግን ለጋራ እዳዉ መክፈያ የጋራ ንብረት ባልበቃ ግዜ ብቻ ስለመሆኑ ህጉ ገደብ ጥሏል፡፡
በዚህም መብት ጠያቂዉ 3ኛ ወገን ጥያቄ ባነሳ ግዜ ተጋቢዎች የግን ንብረታቸዉ እንዳይነካ ና በጋራ ንብረታቸዉ ላይ ብቻ የፍርድ አፈፃፀሙ እንዲቀጥል መቃወምን (Benefit of Discussion ) ህጉ የፈቀደ ይመስላል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዕዳዉ ለትዳር ጥቅም የዋለ እዳ ነዉ ስንል የእዳዎቹ አይነት በተመለከተ ከቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 71 ድንጋጌ አንፃር፡-ለባል እና ሚስት እንዲሁም ለልጆቻቸዉ የእለት ኑሮ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ለማሟላት የተገባ እዳ የሆነ እንደሆነ፤ባል ወይም ሚስት ቀለብ ለመስጠት ያለባቸዉን ግዴታ ለመወጣት የተደረጉ ወጪዎች እንዲሁም ከባል እና ከሚስት በአንደኛዉ ወይም በዕዳ ጠያቂዉ አመልካችነት ለትዳር ጥቅም ስለመሆኑ ፍ/ቤቱ የተቀበለዉ ሌላ ዕዳ ሲሆን ዕዳዉ የጋራ እዳ ተብሎ የሚወሰድ መሆን እንገነዘባለን፡፡
መዉጫ፡-
በሀገራችን፤በተሻሻለዉ የፌደራሉ የቤተሰብ ህግ ለሶስት ዓይነት የጋብቻ ማስፈፀሚያ ስርዓቶች እውቅና ተሰጥቷል፡፡ በክብር መዝገብ ሹም ፊት፤በባህል መሰረት እንዲሁም በኃይማኖት ስርዓት መሰረት የሚፈፀም ጋብቻ መሆናቸዉን ተመልክተናል፡፡
በእነዚህ ስርዓቶ መሰረት የተፈፀመ ጋብቻ (ጋብቻ ህጋዊ ተግባር እንደመሆኑ) በዉጤት ደረጃ የቤተሰብ ህጉ በሚፈቅደዉ አግባብ ተጋቢዎች ንብረት በማፍራት፤በማስተዳደር እና ጋብቻዉ ያልሰመረ እንደሆነ ከፍቺ ቡኃላ በክፍፍል ወቅት እኩል መብት ያላቸዉ መሆኑን እንረዳለን፡፡ በትዳር የተጣመሩ፤ወደ ፊት ሊጣመሩ ያሰቡ በሙሉ እነዚህን መሰረታዊ ነጥቦች ባለሞያ ጋር በመቅረብ መረዳት አስፈላጊ ይሆናል፡፡

7 months ago