Logo
FIDEL POST NEWS
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አዲስ ባወጣው መመሪያ ቁጥር NBE/INT/13/2026 መሠረት፣ ባንኮች የሚሰጡት የቁጠባ እና የብድር ወለድ ተመን ከዚህ በኋላ በገበያ ፍላጎት እና አቅርቦት ላይ ተመስርቶ በየባንኮቹ እንዲወሰን አዝዟል።

​📌 ዋና ዋና ነጥቦች፦
​የቁጠባ ወለድ ተመን (Saving Rate): ከዚህ ቀደም ብሄራዊ ባንክ ያስቀምጠው የነበረው ዝቅተኛ የቁጠባ ወለድ ተመን ቀርቶ፣ እያንዳንዱ ባንክ እንደ ፍላጎቱ የራሱን የቁጠባ ወለድ ተመን ይወስናል።

​የጊዜ ገደብ ተቀማጭ (Time Deposit): ባንኮች ለጊዜ ገደብ ተቀማጭ የሚከፍሉትን የወለድ መጠን ራሳቸው በነፃነት ይወስናሉ።

​የዳይሬክተሮች ቦርድ ኃላፊነት: የእያንዳንዱ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የወለድ መጠኑን በጽሁፍ የመወሰን እና ግልጽ የሆነ አሰራር የመዘርጋት ኃላፊነት ተጥሎበታል።

​አድልዎ መከልከሉ: ባንኮች ለተመሳሳይ የቁጠባ ዘርፍ ደንበኞች እኩል የሆነ የወለድ ተመን መተግበር አለባቸው፤ አድልዎ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

​💡 ይህ ምን ማለት ነው?
ባንኮች ደንበኞችን ለመሳብ የተሻለ የወለድ መጠን በማቅረብ እርስ በርሳቸው እንዲወዳደሩ በር ይከፍታል። ይህም የሀገሪቱን የፋይናንስ መረጋጋት እና የኢኮኖሚ እድገት ለማፋጠን የታለመ መሆኑ ተገልጿል።

​መመሪያው በኢትዮጵያ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ሁሉም ባንኮች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.