Logo
FIDEL POST NEWS
ሃማስ የጋዛን አስተዳደር ለገለልተኛ አካል አሳልፎ ለመስጠት መስማማቱን አስታወቀ

​የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሃማስ በጋዛ ሰርጥ ያለውን አስተዳደራዊ ኃላፊነት ሙሉ በሙሉ ለገለልተኛ ኮሚቴ ለማስረከብ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ። ቡድኑ በወደፊቱ የጋዛ አስተዳደር ውስጥ ምንም ዓይነት የሥልጣን ድርሻ እንደማይኖረውም አስታውቋል።

​ ሃማስ ጋዛን በጊዜያዊነት ለሚያስተዳድሩና ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ለሆኑ ባለሙያዎች (Technocrats) ቦታውን ለመልቀቅ መወሰኑን የቡድኑ ቃል አቀባይ ሀዜም ቃሰም ተናግረዋል።

​ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥለው ሳምንት የጋዛን የሰላም ዕቅድ ሁለተኛ ምዕራፍ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዕቅዱ የጋዛ "የሰላም ምክር ቤት" ማቋቋምን፣ የእስራኤል ጦር እንዲወጣ ማድረግንና ሃማስን ትጥቅ ማስፈታትን ያካትታል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት እስከ 2027 መጨረሻ ድረስ በጋዛ የሚቆይ ጊዜያዊ ዓለም አቀፍ የሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲሰማራ ወስኗል።

ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ ተኩስ አቁም ቢታወጅም፣ አሁንም ድረስ አልፎ አልፎ በሚከሰቱ ጥቃቶች የሰዎች ሕይወት እያለፈ ይገኛል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት በጋዛ ጦርነት ከ71 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸው ይታወሳል።
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.