ትራምፕ አሜሪካ ከቬንዙዌላ ከ30 እስከ 50 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ እንደምታገኝ ገለጹ
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማክሰኞ ዕለት በማህበራዊ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መረጃ በቬንዙዌላ የሚገኙ "ጊዜያዊ ባለስልጣናት" ከ30 እስከ 50 ሚሊዮን በርሜል የሚገመት "ከፍተኛ ጥራት ያለው" ነዳጅ በገበያ ዋጋ ለአሜሪካ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል።
ይህ ማስታወቂያ የተሰማው በካራካስ የሚገኙ ባለስልጣናት፤ ኒኮላስ ማዱሮን በቁጥጥር ስር ለማዋልና በዕጽ ዝውውር ክስ ለመመስረት ወደ አሜሪካ ለመውሰድ በተካሄደው የአሜሪካ ወታደራዊ ዘመቻ ቢያንስ 24 የቬንዙዌላ የጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ካሳወቁ በኋላ ነው።
ትራምፕ በ "Truth Social" ገጻቸው ላይ እንደገለጹት ነዳጁ በማከማቻ መርከቦች ተጭኖ በቀጥታ አሜሪካ በሚገኙ የመርከብ ማቆሚያዎች ይራገፋል።
ገንዘቡ በፕሬዝዳንትነት በእሳቸው ቁጥጥር ስር እንደሚሆንና ይህም የቬንዙዌላንና የአሜሪካን ሕዝብ ለመጥቀም እንደሚውል ገልጸዋል።
በተጨማሪም ዋይት ሃውስ (White House) አርብ ዕለት ከነዳጅ ኩባንያዎች ኃላፊዎች ጋር በኦቫል ኦፊስ (Oval Office) ስብሰባ እያዘጋጀ ሲሆን የኤክሶን (Exxon) የቼቭሮን (Chevron) እና የኮኖኮ ፊሊፕስ (ConocoPhillips) ተወካዮች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በዕለቱ ቀደም ብሎ የቬንዙዌላ ባለስልጣናት በማዱሮ ወረራ ወቅት የሞቱትን ሰዎች ቁጥር ይፋ አድርገዋል።
የሀገሪቱ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዴልሲ ሮድሪጌዝ በትራምፕ ማስጠንቀቂያ ላይ ተቃውሞዋን አሰምታለች።
ትራምፕ ቀደም ብለው ሮድሪጌዝ "ትክክለኛውን ነገር ካላደረገች" እና ቬንዙዌላን ከአሜሪካ ጥቅም ጋር በሚስማማ መልኩ ካልለወጠች ከማዱሮ የከፋ እጣ ፈንታ እንደሚገጥማት አስጠንቅቀው ነበር።
ሮድሪጌዝ ግን እጣ ፈንታዬ የሚወሰነው በእነሱ ሳይሆን በእግዚአብሔር ነው ስትል ምላሽ ሰጥታለች።
የቬንዙዌላው ጠቅላይ አቃቤ ህግ ታሬክ ዊሊያም ሳብ በካራካስ በተፈጸመው ጥቃት "በደርዘን የሚቆጠሩ" የጸጥታ አባላትና ሲቪሎች መገደላቸውን ገልጸው ድርጊቱን "የጦር ወንጀል" ሲሉ ጠርተውታል።
ከዚህ በተጨማሪም የኩባ መንግስት በቬንዙዌላ ሲሰሩ የነበሩ 32 የኩባ ወታደራዊና የፖሊስ መኮንኖች በጥቃቱ መገደላቸውን አረጋግጧል።
እንደ ፔንታገን መረጃ ከሆነ ሰባት የአሜሪካ ወታደሮች በጥቃቱ ወቅት የቆሰሉ ሲሆን፣ አምስቱ ወደ ስራ ተመልሰዋል ሁለቱ ደግሞ በህክምና ላይ ይገኛሉ።
ማዱሮ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ለቀናት ጭር ብለው የነበሩት የካራካስ ጎዳናዎች፣ መንግስት ባዘጋጀው የድጋፍ ሰልፍ ላይ የሀገሪቱን ሰንደቅ ዓላማ በያዙና ሀገራዊ ሙዚቃዎችን በሚያደምጡ ሰዎች ለአጭር ጊዜ ተሞልተው ውለዋል።
የቬንዙዌላ ጦር ባወጣው መግለጫ "የፈሰሰው ደማቸው በቀልን ሳይሆን ፍትህንና ጥንካሬን ይጠይቃል" ብሏል።

5 months ago