Logo
YenetaTube
ለዓለም አቀፍ ህግ ተገዢ ሁኑ - የአፍሪካ ህብረት

በቬንዙዌላ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ከአፍሪካ ህብረት የተሰጠ መግለጫ

የአፍሪካ ህብረት በቦሊቫሪያን የቬንዙዌላ ሪፐብሊክ ውስጥ እየታዩ ያሉ የቅርብ ጊዜ ክስተቶችን፣ የሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት ክቡር ሚስተር ኒኮላስ ማዱሮ መታገታቸውን እና በቬንዙዌላ ተቋማት ላይ የተሰነዘሩ ወታደራዊ ጥቃቶችን በተመለከተ የሚወጡ ዘገባዎችን በከፍተኛ ስጋት እየተከታተለ ይገኛል።

የአፍሪካ ህብረት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር ላይ በሰፈረው መሠረት ለዓለም አቀፍ ህግ መሰረታዊ መርሆዎች፣ ለሀገራት ሉዓላዊነት ክብር፣ ለግዛታዊ አንድነት እንዲሁም ለህዝቦች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት ዳግም ያረጋግጣል።

የአፍሪካ ህብረት በሀገራት መካከል በመልካም ጉረቤትነት፣ በትብብር እና በሰላማዊ አብሮ መኖር መንፈስ፤ ለውይይት፣ ለግጭቶች ሰላማዊ አፈታት እንዲሁም ለህገ-መንግስታዊ እና ተቋማዊ ማዕቀፎች ክብር መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ያሰምርበታል።

የአፍሪካ ህብረት በቬንዙዌላ እየታዩ ያሉ ውስብስብ የውስጥ ተግዳሮቶች ዘላቂ መፍትሄ ሊያገኙ የሚችሉት በራሳቸው በቬንዙዌላውያን መካከል በሚደረግ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት ብቻ መሆኑን ያሳስባል።

የአፍሪካ ህብረት ከቬንዙዌላ ህዝብ ጋር ያለውን አጋርነት በመግለጽ፤ በሀገራት እና በግዛቶች መካከል ሰላምን፣ መረጋጋትን እና የጋራ ክብርን ለማስፈን ያለውን ቁርጠኝነት ይገልጻል።

የአፍሪካ ህብረት የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ሁኔታው እንዳይባባስ ለመከላከል እንዲሁም የቀጠናውን ሰላም እና መረጋጋት ለመጠበቅ ሲሉ ራሳቸውን እንዲገቱ፣ በሃላፊነት ስሜት እንዲንቀሳቀሱ እና ለዓለም አቀፍ ህግ ተገዢ እንዲሆኑ ጥሪውን ያቀርባል።

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.