Logo
FIDEL POST NEWS
27 ሚስቶች በአንድ ቀን ያገባው ሙዚቀኛ

የአፍሮ ቢት ፈጣሪ ፌላ ኩቲ በፈረንጆቹ በ1978 በአንድ ቀን ውስጥ 27 ሴቶችን ማግባቱ በሙዚቃ ከአስገራሚ ታሪኮች አንዱ ነው።

በወቅቱ የየናይጄሪያ ወታደራዊ መንግስት የፌላን መኖሪያ በወረረበት ወቅት አብረውት የነበሩትን ሴት ድምፃውያን እና ዳንሰኞች "ሴተኛ አዳሪዎች " በማለት ያዋርዷቸው ነበር።

ፌላ እነዚህን ሴቶች በህብረተሰቡ ዘንድ ክብርና "የሚስትነት" ማዕረግ እንዲኖራቸው ነው ያገባኋቸው ብሏል።

​ፌላ በአንድ ሆቴል ውስጥ 12 የባህላዊ እምነት ካህናትን በመጥራት ሰርጉን አከናወነ።

27 ሴቶችም በመፈረም ሚስት መሆናቸውን ተስማሙ።

​​"ጋብቻ ቅናትን እና የባለቤትነት ስሜትን ስለሚፈጥር፣ ማንም ወንድ በሴት ላይ ስልጣን ሊኖረው አይገባም" በሚል በ1986 ፌላ ሁሉንም ሚስቶቹን በአንድ ጊዜ ፈትቷቸዋል።
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.