Logo
FIDEL POST NEWS
የወርቁ አይተነውን የ 15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አንቀበልም

አግማስ የመንግስት አጋዥ ድርጅት ነው ሲሉም በመግለጫቸው ገልፀዋል ::
ሙሉ መግለጫው 👇

አግማስ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከኢፌድሪ ሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶት ባለስልጣን ፈቃድ ወስዶ መንቀሳቀስ ከጀመረ አራት አመታትን አስቆጥሯል።

በነዚህ አመታት ውስጥ በርካታ በጎ ተግባራትን የፈጸመና የመንግስት አጋዥም ሆኖ የቆየ ድርጅት ነው። በተለይም ተፈናቃይ ወገኖች ጋር በተያያዘ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በእለት ደራሽ ድጋፍና በቅርቡ ደግሞ በደቡብ ወሎ ሀርቡና ደጋን መጠለያ ካምፖች የዘላቂ መፍትሄ መርህን በመከተል በርካታ ወገኖችን እያደራጀ ወደ ስራ አስገብቷል። አግማስ ኢትዮጵያ እያንዳንዱን ስራዎቹን ሲሰራ በየአካባቢው ከሚገኙ የመንግስት መዋቅር ጋር የፕሮጀክት ስምምነት ( project Agreement) በመፈራረም ነው።

ከክልልም ይሁን ከፌደራል መንግስት በሚቀመጡ አቅጣጫዎች መሰረት እየሰራ የቆየ ሲሆን በዚህም ድርጅታችን ከተለያዩ የዞን ሴክተር መስሪያ ቤቶች የእውቅናና የምስጋና ሰርቲፌኬቶችን ተቀብሏል።

አግማስ ኢትዮጵያ ይህንን በጎ ተግባርና ወገኖችን በዘላቂነት ወደ ስራ የማስገባት እንቅስቃሴውን ለመደገፍ ያለመ የቀጥታ ስርጭት ( online) የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላለፉት ስድስት  ቀናት ያደረገ ሲሆን በዚህ ፕሮግራም ላይም አንዳንድ ከድርጅታችን መርህ ጋር አብረው የማይሄዱ አካሄዶችን አይተናል።

ድርጅታችን ከፖለቲካ ከዘርና ሀይማኖት የጸዳና ገለልተኛ ሆኖ የሚሰራ በመሆኑ ምንም አይነት የፖለቲካም ይሁን ሌላ አላማ ካለው ግለሰብም ይሁን ድርጅት ድጋፍን የማይቀበል መሆኑንም ለማረጋገጥ እንወዳለን።

በዚህም መሰረት እንድህ አይነት አመለካከት ያላቸው ጉዳዮን ከድርጅታችን ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው በማረጋገጥ የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብራችንንም በይፋ ማጠናቀቅና መዝጋታችንን እንገልጻለን።
8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.