Logo
Getu Temesgen
አነጋጋሪው በሽፍንፍን እስከ 82% የዋጋ ጭማሪ የተደረገበት የሳፋሪኮም ነገር
#ethiopia | ትላንት ታህሳስ 14 ቀን ሳፋሪኮም በማህበራዊ ሚዲያ ባሰራጨው የእንግሊዘኛ ማስታወቂያ ዝርዝር ሳይገልፅ የዴታ ጥቅል ላይ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል።

ጉዳዩም ብዙዎች እያነጋገረ ሲሆን በተለይ ለወትሮው ትንሽ ሲናገር አይደለም የአገር ውስጥ የውጭ ሚዲያን ቀልብ የሚገዛው ግዙፉ ኩባንያ ትላንት ይፋ ያደረገው የጭማሪ መግለጫው ምንም ትኩረት አለመሳቡ ዘርፉን የሚከታተሉትን አስገርሟል።

ሌላው ቢቀር የማህበራዊ ሚዲያን መሰረት ያደረጉ ዜና ዘጋቢዎች ስለጭማሪው ያን ያህል ሳይናገሩ አልፈውታል።

ቀላል የማይባል ጭማሪ ነው የተደረገው የሚሉት ውሰጥ አዋቂዎች ሳፋሪኮም ዝርዝሩን ለምን አላወጣም ሲሉ ጥያቄ አንስተዋል።

ስለጭማሪው ለደንበኞች በአግባቡ አላስታወቀም ይልቁንም በማህበራዊ ሚዲያ በእንግሊዘኛ የተሸፋፈነ መግለጫ ነው ብቻ ነው ያወጣው ሲሉ ነው የገለፁት።

ጭማሪው ይፋ ባይደረግም እስከ 82 በመቶ እንደሚደርስ ቅዳሜ ገበያ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

በዚህም መሰረት ዝቅተኛ የሚባለው የዋጋ ጭማሪ ለወርሃዊ የ300 ብር ዋጋ ላለው ጥቅል የተደረገው ሲሆን። ይሄም በ300 ብር ይገዛ የነበረው 6 ጂቢ ኢንተርኔት ወደ 5 ጂቢ የወረደበት ነው።

ከዛ በዘለል ሁሉም በሚባል ደረጃ የእለት፣ ሳምንት እና ወርሃዊ ጥቅሎች በጠቅላላው ከ50 በመቶ እስከ 82 በመቶ ጭማሪ የተደረገባቸው ናቸው። #ቅዳሜገበያ #etbusinessview

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.