በአፍሪካ ዋንጫ ዙሪያ...
ሞሮኮ እና አልጄሪያ ከወዲሁ ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል
#ethiopia | ሁለቱ ጎረቤት ሀገራት ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ሽኩቻ እንዳለባቸው ይታወቃል።
በሞሮኮ ደቡባዊ የሀገሪቱን ክፍል በመገንጠል ነፃ አወጣለሁ በሚል ከመንግሥት ጋር ግጭት ውስጥ የገባ "Polisario" የተባለ የአማፂያን ቡድን አለ።
የሀገሪቱ መንግስትም "አልጄሪያ ለዚህ ተገንጣይ ወንበዴ የገንዘብ፣ የጦር መሳሪያ እና የመጠለያ ድጋፍ ታደርጋለች" በሚል በተደጋጋሚ ጊዜያት ሲከስ ይሰማል።
ከዛም አልፈው ግጭት ውስጥ ሁሉ ገብተው ነበር። የየብሱ አልበቃ ብሏቸው አንዳቸው የሌላኛቸውን የአየር ክልል የማይጠቀሙ ኩርፈኞች ከሆኑ ሰነባብተዋል።
ሌላው ቀርቶ ለዚህ የአፍሪካ ዋንጫ እንኳን የአልጄሪያ ብ/ቡድን ሞሮኮ የደረሰው በሌላ ሀገር የአየር ክልል ተጠቅሞ ነው። እዛ ከደረሱ በኋላም የታዩት ነገሮች በሁለቱ መካከል ያለውን ጡዘት ጨምሮታል።
ሞሮኮ እንደ አዘጋጅ ሀገር ሁሉንም ተሳታፊ ሀገራት በተቀበለችበት መንገድ የአልጄሪያን ብ/ቡድንም በሳምንቱ መጀመሪያ በድምቀት ተቀብላለች።
አልጄሪያዎች በበኩላቸው በአፀፋው ባሳዩት ነገር ወቀሳ እየደረሰባቸው ነው።
የበረሃ ቀበሮዎቹ በተያዘላቸው ሆቴል እንደደረሱ ያደረጉት የመጀመሪያ ስራቸው በየግድግዳዎቹ የሚገኙትን የንጉሥ ሞሀመድ 6ኛ ፎቶዎችን በሙሉ በመጋረጃ መሸፈን ነው።
እኚህ ንጉስ ደግሞ በሞሮኳውያን ልብ ውስጥ ልዩ ቦታ ያላቸው ናቸው።
የሀገሪቱ ሚዲያዎች በበኩላቸው ብ/ቡድናቸውን በተመለከተ ዜና በሚሰሩበት ወቅት የሞሮኮን ካርታ ሲያሳዩ በአልጄሪያ ይደገፋል ተብሎ የሚጠረጠረው የ"Polisario" አማፂ ቡድን የሚታገልበትን የደቡባዊ የሀገሪቱን ክፍል እየቆረጡ ነው።
ይህ አይነቱ ድርጊት በሞሮኳውያን ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።
ይህንንም ተከትሎ አልጄሪያ ጨዋታ በሚኖራት ቀናት ረብሻ እንዳይነሳ ተፈርቷል።
የበረሃ ቀበሮዎቹ በምድብ 5 ከቡርኪናፋሶ፣ ጊኒ እና ሱዳን ጋር ተደልድለዋል ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል።

8 months ago