Logo
SeledaPost
የገንዘብ ሚኒስቴር ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የግብር ጫና ለመቀነስ በማሰብ፣ በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተሞች ዋጋቸው ከአንድ ሚሊዮን ብር በታች የሆኑ ንብረቶች ከንብረት ግብር ነጻ እንዲሆኑ ወሰነ።

ገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ለክልል እና ለከተማ አስተዳደሮች ባስተላለፉት መመሪያ መሰረት፣ ከግብር ነጻ የሆነው የንብረት ዋጋ ጣሪያ እንደ ከተሞቹ ደረጃ ይለያያል፡-

• በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ - ከአንድ ሚሊዮን ብር በታች፣
• በሌሎች ማዘጋጃ ቤት ባላቸው ከተሞች - ከ250,000 ብር በታች፣ እንዲሁም
• በታዳጊ ከተሞች ከ100,000 ብር በታች ዋጋ ያላቸው ንብረቶች ግብር አይከፍሉም።

"ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች" ተብለው የተለዩት፣ በኢኮኖሚ ችግር ውስጥ እንዳሉ በአካባቢው የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊዎች የተረጋገጠላቸው እና ዓመታዊ ገቢያቸው ከሀገራዊ የነፍስ ወከፍ ገቢ ግማሽ  በታች የሆኑ ናቸው።

በፓርላማ የጸደቀውን አዋጅ መሰረት በማድረግ በሚዘጋጀው የክልሎች ህግ፤ ለግብር ስሌት የሚወሰደው የንብረት ዋጋ፣ የንብረቱ ትክክለኛ የገበያ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) ብቻ ይሆናል። የግብር መጠኑም (Tax rate) ከ0.1 በመቶ እስከ 10 በመቶ ባለው ክልል ውስጥ የሚወሰን ይሆናል።

በተጨማሪም የሃይማኖት ተቋማት መገልገያዎች፣ የመቃብር ስፍራዎች፣ የህዝብ መንገዶች፣ ፓርኮች፣ ቅርሶች እና ለህዝብ ነጻ የማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ንብረቶች ከዚህ ግብር ነጻ መደረጋቸው በመመሪያው ተካቷል።

seledadotio
seledadotio
8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.