ዶ/ር ቴድሮስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ምስጋና አቀረቡ
በ'የደራው መጽሔት
#ethiopia | የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ባህላዊ ሕክምናን በዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ውስጥ የላቀ ቦታ እንዲይዝ ላደረጉት አስተዋጽኦ ልባዊ ምስጋናቸውን ገልፀዋል።
ዶ/ር ቴድሮስ በማህበራዊ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ህንድ በጠቅላይ ሚኒስትሩ መሪነት በጤናው ዘርፍ እያሳየች ያለውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።
ለዚህም እንደ ማሳያ የጠቀሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
* የአዩሽ (Ayush) ሚኒስቴር መቋቋም፦ ባህላዊ ሕክምናን በሳይንሳዊ መንገድ ለማሳደግና ለማስተዋወቅ የተቋቋመው ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ለዘርፉ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።
* የዓለም አቀፍ የባህላዊ ሕክምና ማዕከል፦ በህንድ ጃምጋር (Jamnagar) ከተማ የዓለም ጤና ድርጅት የባህላዊ ሕክምና ማዕከል እንዲቋቋም ህንድ ላደረገችው ከፍተኛ ድጋፍ አድናቆታቸውን ችረዋል።
የህንድ ተሞክሮ ጥንታዊ ወጎች ከዘመናዊ ፈጠራዎች ጋር፣ እንዲሁም የታሪክ ቅርስ ከሳይንስ ጋር ተቀናጅተው ሊራመዱ እንደሚችሉ በተግባር ያሳየ መሆኑን ጠቁመዋል።
በመጨረሻም፣ ዶ/ር ቴድሮስ የጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲን "አንድ ምድር፣ አንድ ጤና" (One Earth, One Health) የሚለውን መርህ እንደሚጋሩና ለዚህም ስኬት አብረው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
የደራው መጽሔት
''ፀሐይ አትጠልቅም''

6 months ago