"ባህላዊ ሕክምና ያለፈ ታሪክ አይደለም" ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም
#ethiopia | የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በሕንድ ኒው ዴሊ ባካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ፣ ባህላዊ ሕክምናን ከዘመናዊው ሳይንስ ጋር ለማገናኘት "ሰው ሰራሽ አስተውሎት" (AI) ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት አስታውቋል።
ይህ ስትራቴጂ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የሚታደገውን የባህላዊ መድኃኒት ዘርፍ፣ በሳይንሳዊ ምዘና እና በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ ያለመ ነው።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር፣ "ባህላዊ ሕክምና ያለፈ ነገር አይደለም፤ ይልቁንም በየሀገራቱ ያለው ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል" ሲሉ ገልጸዋል።
በጉባኤው ላይ የተገኙት የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በበኩላቸው፣ ዘርፉ ያለውን እምቅ አቅም ወደ ሳይንሳዊ ምርምር ለመቀየር ቴክኖሎጂ ወሳኝ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው፣ በ90 በመቶ ከሚሆኑት አባል ሀገራት ውስጥ ከ40 እስከ 90 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ባህላዊ ሕክምናን ይጠቀማል።
ከዚህም በላይ፣ ግማሽ ያህሉ የዓለም ህዝብ ዘመናዊ የጤና አማራጮችን ባለማግኘቱ ሙሉ በሙሉ ጥገኛ የሆነው በባህላዊ መድኃኒቶች ላይ ነው።
ይሁን እንጂ መድኃኒቶቹ በቂ ሳይንሳዊ ምዘና ስር ባለማለፋቸው ለአጠቃቀም አዳጋች ሆነው ቆይተዋል ተብሏል።
ይህንን ለመቅረፍም የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እጅግ ውስብስብ የሆኑ የእፅዋት ሥርዓቶችን እና በውስጣቸው ያሉ የፈውስ ኬሚካሎችን በፍጥነት ለመለየት ያስችላል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።
በዚህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይም በየሀገራቱ የተበታተኑ እና ያልተደራጁ የባህላዊ መድኃኒት መረጃዎችን AI በመጠቀም ወደ አንድ ወጥ ሳይንሳዊ ቋንቋ መቀየር እንደሚቻል ተመልክቷል።
ከእፅዋት የሚገኙ ዘመናዊ መድኃኒቶችን ለማግኘት የሚፈጀውን ከ10 እስከ 15 ዓመታት እድሜም፣ AI በመጠቀም ወደ ጥቂት ዓመታት ማሳጠር እንደሚቻል የዘርፉ ተመራማሪዎች በጉባኤው አስረድተዋል።
ሆኖም ግን በጉባዔው ስጋቶች የተንጸባረቁ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አንዱ የባለቤትነት መብትን ማስጠበቅ (Intellectual Property) ላይ ያተኮረ ነው።
AI መረጃዎችን በሚሰበስብበት ወቅት፣ የባህላዊ እውቀት ባለቤት የሆኑ ማኅበረሰቦችን እና የሀገር በቀል እውቀቶችን መብት ማስጠበቅ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት እንደሚገባው በስፋት ተመክሮበታል ተብሏል።
የዓለም ጤና ድርጅት በዘርፉ ያለውን እውቀት ለማሳደግ 1.6 ሚሊዮን ሳይንሳዊ ሪከርዶች ያሉት ዲጂታል የምርምር ክምችት መፍጠሩን ይፋ አድርጓል።
ይህ ግዙፍ መረጃ በAI በመታገዝ ለተመራማሪዎች እና ለጤና ባለሙያዎች ክፍት የሚሆን ሲሆን፣ ባህላዊ መድኃኒቶች ደኅንነታቸው የተጠበቀ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የሚደረገውን ጥረት ይደግፋል ተብሎ ታምኗል ሲል ቲክቫህ ዘግቧል።

6 months ago