የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ወደ አሜሪካ የሚደረጉ የጉዞ ገደቦችን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሰፋ አዲስ አዋጅ ማክሰኞ ዕለት ፈርመዋል።
በዚህ አዋጅ መሠረት፣ ቀደም ሲል 19 የነበሩት ሙሉ ወይም ከፊል የጉዞ እገዳ የተጣለባቸው አገራት ቁጥር ወደ 39 እንዲያድግ ተደርጓል።
ዋይት ሀውስ እንደገለጸው፣ እርምጃው የተወሰደው ዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱት አገራት ተጓዦችን በመለየት እና መረጃን በማጋራት ረገድ "ከፍተኛ የደህንነት ጉድለት" ስላታዩባቸው ነው።
በፕሬዝዳንቱ አዲስ ውሳኔ መሠረት ሰባት አገራት—ላኦስ፣ ሴራሊዮን፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ማሊ፣ ኒጀር፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶሪያ—በሙሉ የጉዞ እገዳ ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል።
በተጨማሪም እንደ ናይጄሪያ፣ ታንዛኒያ፣ ሴኔጋል እና ዛምቢያ ያሉ 15 አገራት አዲስ የከፊል እገዳ ተጥሎባቸዋል። አዋጁ ከሀገራቱ በተጨማሪ በየፍልስጤም ባለሥልጣን የጉዞ ሰነድ በሚጠቀሙ ግለሰቦች ላይም ገደብ ጥሏል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህንን ጥብቅ እርምጃ የወሰዱት በዋሽንግተን ዲሲ አንድ የብሔራዊ ጥበቃ አባል በአፍጋኒስታን ተወላጅ መገደሉን ተከትሎ የኢሚግሬሽን ቁጥጥሩን ለማጠናከር በሚያደርጉት ጥረት አካል መሆኑ ተገልጿል።
ትራምፕ ከጉዞ እገዳው በተጨማሪ የጥገኝነት ጥያቄዎችን ማገዳቸውን እና የተጀመረውን መጠነ ሰፊ ስደተኞችን የማስወጣት ዘመቻ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አዋጁ ሕጋዊ የቋሚ ነዋሪነት ፈቃድ (Green Card) ያላቸውን እና ቀደም ሲል ቪዛ የተሰጣቸውን ግለሰቦች በተመለከተ የተወሰኑ ልዩ ሁኔታዎችን እንደሚፈቅድ ተመልክቷል።
በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ 39 አገራት በእገዳው ዝርዝር ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል እንደ ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ሱዳን ያሉ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ይገኙበታል።
seledadotio

8 months ago