አሻም ቴሌቪዥን ሙሉ በሙሉ ስርጭት ማቆሙን አሳወቀ
📌 ከአሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር የቦርድ አባላት የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል።
#ethiopia | አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ከተመሰረተችበት ባለፉት 8 ዓመታት ጀምሮ በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ በዜናና ወቅታዊ እንዲሁም በመዝናኛ ዝግጅቶች መረጃዎችን በቴሌቪዥን እና በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቿ ስታደርስ ቆይታለች፡፡
ይሁን እንጂ አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ስራዋን ለመቀጠል አቅም ስለሌላት በቴሌቪዥንም ሆነ በየትኛውም የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቿ ከዛሬ ታህሳስ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በይፋ ስርጭት ማቆሟን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ስለሆነም ከተጠቀሰው ጊዜ ጀምሮ የአሻም ሚዲያ መታወቂያ በመያዝ ወይም የሚዲያዋን ሎጎ በመጠቀም በየትኛውም ሁነት (Event) ፣ በእቅድ ዜና ወይም ፕሮግራም ፣ በስልጠና መድረክ ፣ ቃለ-መጠይቅ እና በመሰል ጉዳዮች ላይ የሚገኙ (የሚሳተፉ) ባለሞያዎች የሚዲያ ተቋሙን እንደማይወክሉ ለሁሉም የግልና መንግስታዊ ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች ጭምር በትህትና ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ባለፉት 8 ዓመታት ከአሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ጋር አብራችሁ ለዘለቃችሁ ለውድ ተመልካቶቻችንና ተከታታዮቻችን ልባዊ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው፡፡

6 months ago