Logo
YenetaTube
ኢብራሂም ትራኦሬ "ጥሩ መሪ አይደለም"!/ሙሳሊያ ሙዳቫዲ/

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢብራሂም
ትራኦሬ "ጥሩ መሪ አይደለም" ሲሉ መናገራቸው ተሰማ ።

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሳሊያ ሙዳቫዲ ስለ ቡርኪናፋሶ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ ጠንከር ያለ አስተያየት ከሰጡ በኋላ ክርክር አስነስተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የቡርኪናፋሶው ኢብራሂም ትራኦሬ ጥሩ መሪ አይደለም ሲሉ ትችት ሰንዝረዋል፡፡

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሳሊያ ሙዳቫዲ፣ ስለ ቡርኪናፋሶ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ የሰነዘሩት "እውነተኛ መሪ ሽጉጥ በወገቡ ላይ መያዝ ወይም መሳሪያ በጠረጴዛው ላይ ማሳየት አያስፈልገውም ብለዋል። እንደ እርሳቸው ገለጻ፣ አመራር በተቋማት፣ በዲሞክራሲ እና በተጠያቂነት ላይ መገንባት አለበት - በኃይል አይደለም።ብለዋል ።

የሙዳቫዲ ንግግራቸው የመጣው በምዕራብ አፍሪካ የሚገኙ ወታደራዊ መሪዎች በተለይም በወጣቶች ዘንድ በጠንካራ ፀረ-ኢምፔሪያሊዝም አቋማቸው እና በደህንነት ቃል ኪዳናቸው ምክንያት ተወዳጅነትን እያገኙ ባሉበት ወቅት ሲሆን ይህም እያስተቻቸዉ ይገኛል ።

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.