Logo
Getu Temesgen
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለሠዓሊና ቀራጺ በቀለ መኮንን የሙሉ ፕሮፌሰር ማዕረግ ሰጠ

(ይትባረክ ዋለልኝ)
#ethiopia | የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለታዋቂው የሥነጥበብ ባለሙያ ሰዓሊና ቀራጺ በቀለ መኮንን በሥነጥበብ ዘርፍ የሙሉ ፕሮፌሰር ማዕረግ ሰጠ።

በቀለ መኮንን በብዙዎች ዘንድ በቀራጺነት፣ በሰዓሊነት እና በገጣሚነት የሚታወቅ መምህርና የጥበብ ሰው ነው። ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን ሀገራችን ኢትዮጵያ ባሻገር አፍሪካን በዓለማቀፍ መድረኮች ላይ መወከል የቻለ ከያኒ ሲሆን በሥነጥበብ ዘርፍ በሃገራችን የመጀመሪያው ሙሉ ፕሮፌሰር ያገኘ ተመራማሪ ነው።

የፊታችን ማክሰኞ ዩንቨርሲቲው የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ማዕረጉ ይቀበላል::

እንኳን ደስ አለህ በቀለ መኮንን::

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.