Logo
Getu Temesgen
ለሠዓሊና ቀራፂ በቀለ መኮንን(ተ/ፕ) የአክብሮትና የምስጋና ፕሮግራም ተደረገለት

(ይትባረክ ዋለልኝ)
#ethiopia | "የአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ዳግም ትንሳኤን ለማሳካት ድልድይ ሆነው ስለጀመሩት እናመሰግናለን " በማለት ለሠዓሊና ቀራጺ በቀለ መኮንን (ተ/ፕ ) ዛሬ ህዳር 4 ቀን 2018 ዓ.ም የአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት የቀድሞ ተማሪዎች በት/ቤቱ የአክብሮትና የምስጋና ፕሮግራም ዛሬ አደረጉለት::

በጀርመን ሐገር ፍራንክፈርት ከተማ ከሚገኝው የሥ ነጥበብ ዩንቨርሲቲ ጋር ከአመታት በፊት በቀድሞው የአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ተማሪ በሆነው ሰዓሊ ግርማቸው እና ባለቤቱ ከአለ የሥነ ጥበብና ዲዛይን ት/ቤ ጋር የተጀመረውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ከጅማሮው አንስቶ ብዙ ደክመው ዳር በማድረስ ላደረገው ታላቅ ሐገራዊ ተግባር እና ለአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ዳግም ትንሳኤን ለማሳካት ድልድይ ሆነው ስለጀመሩት እናመሰግናለን በማለት ለሠዓሊና ቀራጺ በቀለ መኮንን (ተ/ፕ ) የአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት የቀድሞ ተማሪዎች የአክብሮትና የምስጋና ፕሮግራም ያደረጉለት::

ዛሬ ረፋድ ላይ በአለ ት/ቤት አዳራሽ ውስጥ ለሠዓሊና ቀራጺ በቀለ መኮንን (ተ/ፕ ) በተዘጋጀው የአክብሮትና የምስጋና ፕሮግራም ላይ ሠዓሊና ቀራጺ በቀለ መኮንን (ተ/ፕ ) በጀርመን ፍራንክፈርት ስለነበራቸው ቆይታና ስለተከናወኑት ተግባራት ወደፊት ምን መደረግ እንዳለበት ለታዳሚው ሐሳባቸውን አካፍለዋል::

በተለይም በፍራንክፈርት ቆይታቸው በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሥነጥበብ ባለሙያዎች በማሰባሰብ በጀርመን እና በኢትዮጵያ መካከል የሥነጥበብ የእውቀትና የባህል ልውውጥ እና ከመላው ዓለም ከሚገኙ መሰል ዩንቨርሲቲዎችና ተቋማት ጋር ከግለሰብ ግንኙነት በዘለለ ዘላቂነት ባለው መንገድ በሥነጥበብ ት/ቤቱ በኩል በመሰባሰብ መስራት እንዳለባቸው ገልፀዋል::

በዚህ ፕሮግራም ላይም በሐገር ውስጥና በመላው ዓለም የሚገኙ የአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት የቀድሞ ተማሪዎች ዘላቂነት የሚገናኝበት አንድ ዲጂታል ፕላትፎርም ለመጀመር ና ዘላቂነት ባለው መልኩ የሚገናኙበትና ብዙ የሚሰሩበትን መንገድ ወጥነዋል::

በዚሁ ፕሮግራም ላይ ት/ቤቱ የቀድሞ ተማሪዎች በአልሙኒየምና በእንጨት የተሰራ ፎቶግራፍና የምስጋና ፁሑፍ የተፃፈበትን ግሩም ሥጦታ የአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አገኝሁ አዳነ ለሠዓሊና ቀራጺ በቀለ መኮንን (ተ/ፕ ) አበርክተዋል::

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.